EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 26 May 2016

ዳዊት ሮክፊለር - አንድ የአለም ስርዓት የመመሥረት ሴራ እውነት መሆኑ አረጋገጠ


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ



ዳዊት ሮክፊለር የሃገረ አሜሪካ የሰላቢ እጆች (ኢሉሚናቲ) የክርስትና ኣባት ብንለው ህተት አይሆንም።ይህ ሰው የአለማችን መቶ አመት የዕድሜ ጸጋ ያሳለፈ  ብቸኛው ቢልየነር ነው። 100 አመት የደፈነው ባለፈው 2015  እ.ጎ.አ ወርሃ ሰኔ ነበር።

ሮክፊለር ከሮዝስቻይልድ ጋር የአለማችን ቱጃሮችና ተጽዕኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ የሆኑ የኢሉሚናቲ የደም ሓረግ ያላቸው ቤተ ሰብ ናቸው።ባለፉት 250 አመታት በምድራችን የተካሄዱት ጦሩነቶች በነዚህ ቤተ ሰቦች የገንዘብ ድጋፍ የተጀመሩ ናቸው።በ 1937 እ.ጎ.የሮክፊለር የወንድ አያት የውሃንስ ሮክፊለር የስታንዳርድ ዘይት ( standard oil ) መሥራች ቱጃር ነበር።ብዙ ጊዜ የሮክፊለር ስም ከሃብት፣ ስልጣን፣ ፖለቲካ፣ ገንዘብ ነክ፣ ዲፕሎማሲ፣ የማሪዋና ክልከላ፣ እንግዳ ፍጥረቶች፣ ዩፎና (UFO) ሴራ ጋር ተያይዞ ይነሳል።

ከሴራዎቹ መካከልም አንድ የአለም ስርዓት መመሥረት ጉዳይ አንዱና ዋነኛው ነው።የኢሉሚናቲ አጋርና መሳርያ የሆኑት የሰወሥትዮሽ ውል (Trilateral commission) የውጭ ግንኝነት ማዕከልና የቢልደርበርግ ግሩፕ በሮክፊለር የተመሰረቱ ናቸው።ይፋ ያልሆነው የአሜሪካ የቀድሞው የንጉሳዊ ቤተ ሰብ አባል ሮክፊለር በአንድ የአለም ስርዓትን የመመሥረት ሴራ በሚቀርብበት ክስ ምክንያት ጥፋተኛ የምባል ከሆነ የምቀበለውና የምኮራበት ነው በማለት ይገልጻል።

ግንቦት 18,2008 ዓመተ ምሕረት