EAR

አዲስ ነገር

Friday, 6 May 2016

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በዳግመኛው የጣልያን ወረራ ጊዜ ከሃገር የወጡበት ትክክለኛው ምክንያት


·         ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


" የኔ ታሪክ እዚህ ያበቃል።የናንተ ታሪክ እዚህ ይጀምራል።የኢትዮጵያ አንድነት በመጠበቅ ዳር ድንበሯን ማስከበር ካቃታቹ ያንጊዜ የናንተ ታሪክ ይሞታል።የኔ ታሪክ ደግሞ ያኔ ይጀምራል።" ---ቀዳማዊ  ኃይለሥላሴ  

ዛሬ ሚያዝያ  27,2008 ዓመት ምሕረት 75ኛው አርበኞች ቀን እየተከበረ ነው።ከዚህ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ መካነ ድሮች አንዳንድ ከእውነት የራቁና ከዘረኝነትና ታሪክን ለጥላቻ ስብከት በማዋል መነታረክና መሰዳደብ ልምድ ያደረጉ ሰዎች ዳግመኛው የፋሺስት ጣልያን የኢትዮጵያ ወረራ ተከትሎ ክግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ከሃገር የወጡበት ሁኔታ ከእውነታ በወጣ መንገድ ሲጽፉ በማየቴ ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጀት መልስ ለመስጠት እሞክራለው።

አንድ ሰው የሚጽፈው ነገር በተቻለ መጠን ማስረጃን መሠረት ያደረገና አሳማኝ መሆን አለበት ብየ አምናለው።ይህ ካልሆነ ግን በሰሚ ሰሚ የሚነገር የጥላቻና የውሸት አፈ ታሪክ የትም አያደርሰንም።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የጣልያን መንግስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ያለ አግባብ እንደወጋቸው ለሊግ ኦፍ ኔሽን አቤቱታቸው ቢያቀርቡም የአለም መግስታት ግን ጆሮ ዳባ በማለታቸው ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እግዚአብሔር ግን እንደሚፈርድባቸው በመናገር ወደ ሃገራቸው ኢትዮጵያ በመመለስ በላሊበላ ቤተ ክርስትያን የ ሁለት ቀናት የጾምና የጸሎት ሰነ ስርዓት አካሂደዋል።ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከስር ይመልከቱ።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በላሊበላ ቤተ ክርስትያን ያደረጉት የጾማና የጸሎት ሰነ ስርዓት

ከፍተኛ ከሆነ የድካም ስሜት የዕንቅልፍና የምግብ እጥረት በኋላ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሻንጣቸውን በመጠቅለል ግንቦት 5,1936 ዘመናዊና ወቅታዊ የጦር መሣርያ የታጠቀው የጣልያን ጦር ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተረዱ በኋላ የኢትዮጵያ የጦር ዘማቾች የነበሩት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ታሪካዊ የሆነ ስህተት በባዕዳውያን ኢትዮጵያ ላይ እንዳይፈጸም ግርማዊነትዎ ከሃገር እንዲወጡ በነገርዋቸው መሰረት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ባለ ቤታቸው ወይዘሮ መነን ልጆቻቸውን በመያዝ ወደ አውቶሞቢል በመግባት ቀጥሎም ብቸኛው በነበረው የባቡር ሃዲድ በመጠቀም ጅቡቲ ደረሱ።

በወደብ ላይ የተገኝው የጣልያን ጋዜጣ ዘጋቢ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ምስል ለማንሳት ሲሞክር በቦታው በነበሩ ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቅ ተደርጓል።

ሚያዝያ 27,2008 ዓመተ ምሕረት