EAR

አዲስ ነገር

Monday, 20 June 2016

በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል።

·         ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለ ኢትዮጵያዊነት አጥብቄ ስፅፋና ስናገር ለመቃዎም ሲሞክሩ አጋጥሞውኛል።ሆኖም ጥልቅ የሆነውን ኢትዮጵያዊነት በፓለቲካ ሚዛን ስለሚመዝኑት እንጂ አካባብያቸው በጥልቅ ልቦና ለመረዳት ቢሞክሩ መልሱ ያገኙታል።
ስቀጥል ወዳጄ ኢትዬጵያዊነት ሰዎች ያሰመሩት ምድራዊው ድንበር ወይም ካርታ እንዳይመስልህ።ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ነው ጥልቅ ነው ድንቅም ነው።የኢትዬጵያዊነት ማሰርያው የእግዚአብሔርን ልጅነት መቀበል ነው።


የሰው ልጅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው።ይህ ነው የኢትዮጵያዊነት ረቂቅነት።ስለ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ መላው የሰው ልጅ ተነሳ ማለት።እግዚአብሔር ኢትዮጵያን የአለምን መፍረጃ ያደረጋት በዚህ ምክንያት ነው።ኢትዮጵያ እጆችዎ ወደ እግዚአብሔር የምትዘረጋው የተሰጣትን ታቦት በማያዝ ስለ መላው የሰው ልጅ ሃጥያት እንጂ ስለ 100 ሚልዮን ሰዎች ብቻ አይደለም።ክርስቶስ የተሰቀለውና መድሃኒአለም የምንለው መላውን አለም በቸርነቱ ስለ አዳነ ነውና።

የአሁን ጊዜ ትውልድ ግን የዲያብሎስ ተባባሪ በመሆን ኢትዮጵያዊነትን በትግራዋይነት ፤አማራነት ፤ ኦሮሞነት በመመንዘር እውነታው ለመቅበር ይሞክራል።

ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው።

ኢትዮጵያን ይባርክ።