EAR

አዲስ ነገር

Saturday, 9 July 2016

የሶቅራጦስ ሦስቱ ፈተናዎች

·         ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

የፋልስፋና ሰነ ፍጥረት የተካሄደባት ተብላ በምትታመነው ጥንታዊትዋ ሃገረ ግሪክ ከ469 - 399 ከክርስቶስ ልደት በፋት የነበረው ፋላስፋው ሶቅራጦስ ፋልስፋናው በከፍተኛ ሁኔታ ተቀባይነት ባገኘበት ወቅት በአቴንስ ከተማ አደባባይ እየተንቀሳቀሰ ሳለ አንድ ሰው ወደ ሶቅራጦስ በግርምትና አድናቆት እያመራ ሶቅራጦስን እንዲህ ይለዋል።
"ከተማሪዎችህ( ደቀመዛሙርት) ስለ አንድ ምን እንደሰማው ታውቃለህ ?" ይለዋል
ሶቅራጦስ መለሰ" አንድ ጊዜ ቆየኝ ወሬህ ከመቀጠልህ በፊት ፈተና እሰጥሃለው ፈተናው የሦስቱ ፈተና ይባላል።"
"የሦስቱ ፈተና ?"
"አዎ "ቀጠለ ሶቅራጦስ "ስለ ተማሪየ ለኔ ከመናገርህ በፉት ስለምትነግረኝ ነገር እውነተኝነት እርግጠኛ ነህ ?"
"አይደለሁም" ሰውየው ቀጠለ "ከሰዎች ሰምቼ ነው።"
"እሺ ስለምትነግረኝ ነገር እውነት ይሁን ውሸት አታውቅም ማለት ነው።ወደ ሁለተኛው ፈተና እንለፋ ስለ ተማሪየ የምትነግረኝ በጎ ነገር ነው መጥፎ?"
"በጎ አይደለም መጥፎ ነው።" በማለት መለሰ
ሶቅራጦስ በመቀጠል "ታድያ ለምን ስለ ተማሪየ መጥፎ ነገር ልትነግረኝ ፈለክ ለዚያውም እውነት መሆኑ ያልተረጋገጠ?"
ሰውየው ትክሻውን ነቀነቀ አፈረ።
ሶቅራጠስ ሲቀጥል እንዲህ አለ "ፈተናው መጨረስ አለብህ ስለዚ የመጨረሻው ጥያቄ ስለ ተማሪየ ልትነግረኝ ያሰብከው ነገር ለኔ ይጠቅመኛል?"
"አይጠቅምህም"
"ጥሩ ስለ ተማሪየ ልትነግረኝ ያሰብከው ነገር እውነተኝነቱ ያልተረጋገጠ፤ መጥፎና ለኔ የማይጠቅም ነው።ታድያ ለምን ልትነግረኝ ፈለክ ?"በማለት ንግግሩ ጨረሰ።
ሰውየው ምንም መልስ ሳይሰጥ ህፋረትን ተከናንቦ መንገድ ቀጠለ።
ለሚመለከተው ሁሉ።
ሰላም