·
ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ሃገራችን ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ለየት የሚያደርጋት ስርዓተችዋ የእግዚአብሔር ክብር የሚገልጡና የሚያስቀድሙ መሆናቸው ነው።ከነዚህ መካከልም የምትጠቀምበትት የቀን አቆጣጠር አንዱ ነው።በቀጥታም የወሮቹ ስያሜ የእግዚአብሔርን ክብር የሚያጎሉ ናቸው።የምዕራባውያን የወሮችና የቀን ስያሜ ግን ከዚህ በተቃራኒ የጣኦት አምልኮ የሚገለጽባቸውና በቀጥታ ከአምልኮው ጋር የሚገናኙ ናቸው።ከአራት አመት
በፊትም የካቶሊክ ቤተክርስትያን ፖፕ ፍራንሲስ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ትክክለኛው አቆጣጠር መሆኑ መስክረው
ነበር።የካቶሊክ ቤተክርስትያን የዲያብሎስ (ኢሉሙናቲ) ባርያ መሆንዋ
ይታወቃል።
የኢትዮጵያ የወቅቶች መቀያየር ራሱ የኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ምስክር ነው።አሮጊት አመት አልቆ አዲስ አመት ሲገባ የሚታየው የወቅት ለውጥና የእንቁጣጣሽ አበባ በየቦታው መመልከት ተፈጥሮም ምስክር መሆንዋ ማረጋገጫ ነው።
በመቀጠል የኢትዮጵያና የምዕራባውያን የቀኖችና የወር ስያመዎች ትርጉማቸው እናያለን።
የቀኖች ስያሜ ትርጉም
1.እሑድ - እሑድ፣ እሒዶት ከሚለው ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረገ (የመጀመሪያ ሆነ) ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ስለጀመሩ እሑድ ተብሏል፡፡
2. ሰኑይ - ሰኑይ፣ ሰኑዮት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሁለት አደረገ ማለት ነው፡፡ ለሥነ ፍጥረት ሁለተኛ ስለሆነ ሰኑይ (ሰኞ) ተብሏል፡፡
3.ሠሉስ - ሠልሶ፣ ሠልሶት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ሦስት አደረገ ማለት ነው፡፡ ማግሰኞ ማለት የሰኞ ማግስት ማለት ነው፡፡ ሦስት መባሉም ለሥነ ፍጥረት ሦስተኛ ቀን መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
4. ረቡዕ - ረብዓ፣ ረብዖት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አራት አደረገ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
5.ኀሙስ - ኀምሶ፣ ኀምሶት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን አምስት አደረገ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ለሥነ ፍጥረት አምስተኛ ቀን መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
6.ዐርብ - ዐሪብ፣ ዐሪቦት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው፡፡ ፍጥረታት እሑድ መፈጠር ጀምረው ዓርብ መካተታቸውን (ተፈጥረው መፈፀማቸውን) የሚያስረዳ ነው፡፡
7. ቅዳሜ - ቀዲም፣ ቀዲሞት ከሚል ንዑስ አንቀጽ የተገኘ ሲሆን ሰንበተ ክርስቲያን ከሆነችው ከዕለተ እሑድ ቀድማ ስለምትገኝ ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ) ተብላለች፡፡
የምዕራባውያኑ የቀናት ስያሜ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ስለሌለው ትርጕማቸው ለጣዖታት መታሰብያ የተሰጠ ነው፡፡ ይኸውም እንደሚከተለው ነው፡፡
1. ጹንዳይ – ጹን’ስ ዻይ ፡ የፀሐይ ቀን፣ ፀሐይን የሚያመልኩ ስለሆነ ለአምላካቸው የሰጡት የመታሰብያ ቀን፤
2. ሞንዳይ – ሞኦን’ስ ዻይ ፡ የጨረቃ ቀን፣ ጨረቃን የሚያመልኩ ሰለሆነ ለአምላካቸው የሰጡት የመታሰብያ ቀን፤
3. ጡአስዳይ – ጢኡ’ስ ዻይ ፡ የቲው ቀን፣ ቲው (የጦርነትና የጠፈር አምላክ) ለሚሉት ጣዖት የተሰጠ የመታሰብያን ቀን፤
4.Wአድነስዳይ –
Wኦደን’ስ ዻይ ፡ የወደን ቀን፣ ወደን (የአደን አምላክ) ለሚሉት ጣዖት የተሰጠ የመታሰብያ ቀን፤
5. ጥሁርስዳይ – ጥሆር’ስ ዻይ ፡ የቶር ቀን፣ ቶር (የመብረቅ አምላክ) ለሚሉት ጣዖት የተሰጠ የመታሰብያ ቀን፤
6. ፍሪዳይ – ፍረያ’ስ ዻይ ፡ የፍረያ ቀን፣ ፍረያ (የፍትወትና የውበት አምላክ) ለሚሉት ጣዖት የተሰጠ የመታሰብያ ቀን፤
7. ጻቱርዳይ – ጻቱርን’ስ ዻይ ፡ የሳተርን ቀን፣ ሳተርን (የእርሻ አምላክ) ለሚሉት ጣኦት የተሰጠ የመታሰቢያ ቀን ነው፡፡
የወሮች ስያሜ ትርጉም
1.መስከረም ከረመ ከረመ፥ ምሴተ ክረምት፣ የክረምት መካተቻ
2.ጥቅምት ጠቀመ ጠቀመ፥ ጽጌ መደብ አድርጎ ፍሬ ሲሰጥ
3.ኅዳር ኀደረ አደረ፥ ገበሬ አዝመራዉን ሲጠብቅ ከዱር ስለሚያድር
4.ታኅሳስ ኀሠሠ ፈለገ፥ መረመረ፣ ሰብአ ሰገል ጌታን ፍለጋ በኮከብ እየተመሩ መምጣታቸውን የሚያስረዳ ፨ማቴ።፪፡፩፡፯፨፡፡
5.ጥር ጠየረ መጠቀ፥ ረዘመ፣ ከጥቅመ ሰናዖር ጋር የተያያዘ ነው ፨ዘፍ።፩፩፡፩፡፩፩፨፡፡
6.የካቲት ከተተ ሰበሰበ፥ ገበሬ ምርቱን መሰብሰቡን የሚያስረዳ፡፡
7.መጋቢት መገበ መገበ፥ የመዓልትና የሌሊት ምግብና ትክክል (እኩል) መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
8.ሚያዝያ መሐዘ ሚዝት ፈለገ፤ የሚዛዝት (የሚዜዎች) ወራት፤ ወሩ ጋብቻ ስለሚበዛበት የተሰጠው ስያሜ፡፡
9.ግንቦት ገነባ ገነባ፥ የባቢሎን ግንብ ሳይወር ሁለቱ መቅደሶች በዚህ ወር መመሥረታቸውን የሚያስረዳ ፨፫ነገ።፮፡፩፣ ዕዝ።፫፡፰፡፩፩፨፡፡
10.ሰኔ ሠነየ አማረ፥ የማሣው በዘር መሸፈኑን የሚያስረዳ ነው፡፡
11.ሐምሌ ሐምለ ለመለመ፥ ወሩ የቅጠላቅጠል፣ የልምላሜ ወር መሆኑን የሚያስረዳ
12.ነሐሴ ነሐሰ ሠራ፥ ጨረሰ፣ የመጨረሻ ወር
በምዕራባውያኑ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ስለሌለው የወራቱ ስያሜ እንደ ቀናቱ ሁሉ ለጣዖታት መታሰብያ የተሰጠ ነው፡፡ ይኸውም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1.ጃኑኣርይ – ጃኑስ ሞንጥ ፡ የጃኑስ ወር፣ የኆኀት (የደጅ) አምላክ ተብሎ ለሚታሰብ ጣዖት፤
2.ፈብሩኣርይ – ፈብሩኣ’ስ ሞንጥ ፡ የፌብሯ ወር፣ ሥርየትን የሚሰጥ አምላክ ተብሎ ለሚታሰብ ጣዖት፤
3. ማርጭ – ማርስ’ ሞንጥ ፡ የማርስ ወር፣ የጦርነት አምላክ ተብሎ ለሚታሰብ ጣዖት፤
4.ዓፕሪል – ዓጵሮዲተ’ስ ሞንጥ ፡ የአፍሮዳይት ወር፣ የፍትወትና የውበት አምላክ ተብላ ለምትታሰብ የሴት ጣዖት፤
5. ማይ – ማኢኣ’ስ ሞንጥ ፡ የማያ ወር፣ የስጦታ አምላክ ተብላ ለምትታሰብ ጣዖት፤
6.ጁነ – ጁኖ’ስ ሞንጥ ፡ የጁኖ ወር፣ የጋብቻና ሴቶችን ጥሩ እንዲሆኑ ታደርጋለች ተብላ ለምትታሰብ ሴት ጣዖት፤
7.ጁልይ – ጁሊኡስ’ ሞንጥ ፡ የጁሊዮስ ቄሳር መታሰብያ ወር፤
8.ዓኡጉስት – ዓኡጉስቱስ’ ሞንጥ ፡ የአውግስጦስቀ ቄሳር መታሰብያ ወር፤
9.ጸፕተምበር – ጸፕተም ፡ ሰፕተም፣ ሰባት፣ ሰባተኛ ወር፤
10. ዖችቶበር – ዖችቶ ፡ ኦክቶ፣ ስምንት፣ ስምንተኛ ወር፤
11. ኞቨምበር – ኞቨም ፡ ኖቨም፣ ዘጠኝ፣ ዘጠነኛ ወር፤
12.ዸቸምበር – ዸቸም ፡ ዴሰም፣ ዐሥር፣ ዐሥረኛ ወር በማለት ወራቱን በሙሉ እንደ ቀናቱ ሁሉ ለጣዖታት መታሰብያ አድርገው ይጠሩዋቸዋል፡፡