ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከአንድ ዓመት በፊት በመቐለ ከተማ ወጣቶችን ከሱስ ለማላቀቅ ከመቐለ መካነ አዕምሮ(University) በመተባበር የሚሰራ መቋሚያ ስለተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከራሴ ጋር በማያያዝ ትንሽ ጽሑፍ በመጻፍ እዚሁ የህዋ ሰሌዳ (Website) ላይ ለጥፌ ነበር። ጽሑፉ የመቋሚያ በጎ ስራ ያደነኩበት ቢሆንም ሃይማኖታዊ የሆነ ድብቅ አላማ እንዳይኖረው የሚል ጥርጣሬ እንዳለኝም ጠቁሜ ነበር። (መቋሚያ - ሱስ የምንከላከለውና የሚድን በሽታ ነው።) ይህንን ጥርጣሬየ ሊያረጋግጥልኝ የሚችል መረጃም በተቻለኝ አቅምና መንገድ ለማግኝት ሞክርያለው። ጥርጣሬየም እውነት መሆኑ የሚያረጋግጡ ነገሮችም በቂ ባይሆንም ጥቂት ግን አግኝቻለው።
ኢትዮጵያ ብተደጋጋሚ እንደምገልጸው የሰላቢ እጆች ዋነኛዋ የጥቃት አቅጣጫ ነች።ምክንያቱም እውነተኛው የእግዚአብሔር አምልኮ የሚፈጸምባት ሀገረ እግዚአብሔር በመሆንዋ ነው። ይህንን ጸጋዋ ለማጥፋትና ለመዝረፍ እነዚህ የዲያብሎስ አገልጋዮች ምዕራባውያን የሰይጣን አምላኪዎች የተቻላቸውን መንገድ በመጠቀም ተግባራዊ ለማድረግ ለዘመናት እንቅልፍ ሳይወስዳቸው ሞክሮዋል። ለኢትዩጵያውያን በጎ አሳቢ መስለው በመግባት ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋትና ለመቀየር ሞክረው ለጊዜው የተሳካላቸው ቢመስልም በእግዚአብሔር ረዳትነት ረጂም ጊዜ ሳይወስድ ጠፍተዋል። ቆይተዉም ቢሆን ጦር በማከማቸት እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ህዝበ ኢትዮጵያ ለመውረርና ለመግዛት ቢመጡም አሁንም በእግዚአብሔር ረዳትነት ድል ተደርገው ዕፍረትን አትርፈው ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል። ይህ ሁሉ ቢሆንም
ተዋሕዶን ለማጥፋት አሁንም የሚተኙ አይደሉም። ዲያብሎስ የእግዚአብሔር የሆነውን ለማጥፋት መሞከሩ አይቀርም። የጥቃት መንገዱ ይቀይራል እንጂ።
ኢትዮጵያውያን የሚያጋጥመን ስጋዊ የሆነ ድህነታችን ለነዚህ አካላት ዋነኛው የዕቅዳቸው ማስፈጸምያ መንገድ በመሆን እያገለግለ ነው። ድህነታችን በመጠቀም ለኛ አሳቢና ተቆርቋሪ መስለው በመግባት ባቋቋምዋቸው መንግስታዊ ያልሆኑ የእርዳታ ድርጅቶች (NGO) ባዕድ የሆነው ሃይማኖታቸውን
በኛ ህዝብ ላይ ለማስረጽ ይጠቀሙበታል። ይህ አካሄዳቸዉም ብዙ ለሆዳቸው ያደሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲከተልዋቸው መንገድ ጠርጓል።
ተዋሕዶ ኢትዩጵያና ኢትዮጵያዊነት
እንደማይነጣጠሉ ስለሚያውቁም እነዚህ በሆዳቸው የተገዙ ኢትዮጵያውያን ሰዎች በመጠቀም ተዋሕዶ ተሃድሶ ያስፈልጋታል በማለት ሃይማኖትዋ
በባዕድ ስይጣናዊ አምልኮ ለመቀየር እንቅልፍ አጥተዋል። ይህ አካሄዳቸዉም ብዙ ዕውቀት የሌላቸውና ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎች እንዲያገኙ
ያደርጋቸዋል።
ተሃድሶ በማለት የሚያካሂዱት
እንቅስቃሴም በደምብ በተጠናና የማይደረስበት በሚመስል መንገድ እየሰሩብት ነው።አ ንድ መንገድም በበጎ አድራጎት ሽፋን የተለያዩ
ሀገር በቀል ስያሜና መስራች ሰዎች በማቋቋም ከጀርባ ሃይማኖትን ወደ ፕሮቴስታን የማስቀየር ስራ መስራት ነው።