EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 1 January 2017

ክርስቶስ እንዳለው ይሆናል


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

በዚህ ባለንበት ዘመን በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ በግልጽ የሚታየው ችግር ወይም የፈረሰው ቅጥራችን የሀገራችን በሮችና አጥሮች ሳይሆኑ የኢትዮጵያዊ ማንነታችን እና መገለጫችን የሆነው መንፈሳዊ ማንነታችን ነው፡፡ በምዕራባውያን ፍልስፍና እና ማንነት የተጠመደ እና የተደባለቀ ህይወት ይዘን የእግዚአብሔር ምድር (ሃገረ እግዚአብሔር)  የሆነችውን ሀገራችንን እያረከስናት ነው በዚህ ምክንያትም ቅጥራችንን አፍርሰናል፡፡

ክርስቶስ የስናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ተነቅለህ ወደዛ ሂድ ብትሉት ይሄዳል እንዳለው እኔም እላለሁ፣የጤፍ ቅንጣት የምታህል ተግባር ቢኖራችሁ ይህንን ይህንን የሴራ አለምና ኢትዮጵያዊነትን ለመቅበር የሚንደረደረው ወደዛ ወግድ ብትሉት ይወገዳል።
እየሱስም እንዲህ አላቸው እምነታቹ ጎደሎ ስለሆነ ነው በእውነት እላችሃለው የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነስተህ ሂድ ብትሉት ይሄዳል   የሚሳናቹሁም ምንም ነገር አይኖርም። ---                ማቴዎስ 17:20

ክርስቶስ እንዳለው ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በስሜ ብትሰበሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ ብሏል፤እኔም እላለሁ ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በኢትዮጵያና በነጻነት ስም ብትደራጁ ተግባር በመካከላችሁ ይገኛል፡፡

አንድ ሚሊዮን ወሬ ከማወራት የስናፍንጭ እንዳውም የጤፍ ቅንጣት የሚያህል ተግባር ፍጠሩ!! ትንንሽ ተግባሮች ተጠራቅመው እንዴት ይሆናል ብለን የምናስበውን ነገር ነው መንግሎ ወዲያ የሚጥለው፡፡

እንዲሁም አልአዛር ሞቶ ክርስቶስ እነመቅደላዎ ማርያምን ድንጋዩን አንሱት ሲላቸው ባለማመን ውስጥ ገብተው ነበር ግን ክርስቶስ እመኚ እንጂ ታያለሽ አላልኩስምን አላትና ድንጋዩን አንሱት አለ፡፡ለእነማሪያም፡፡ ለምን አንተ ድንጋይ ተነስ አላለም ብሎ መጠየቅ መልካም ነው፡፡እነማሪያምን ድንጋይ አንሱ እኔ ደግሞ አልአዛርን ከሞት አስነሳዋለሁ ማለቱ ነው፡፡ ይህም ማለት ሁሉም የድርሻው ይስራ፣ ሁላችሁም ያቅማችሁን የምትችሉትን ስሩ፣ እናንተ በአልአዛር ላይ ያለው ድንጋይ ማንሳት ትችላላችሁ እኔ ደግሞ አልአዛርን ከሞት አስነሳዋለሁ እንደማለት ያለ አገላለጽ ነው፡፡ የኢትዮጵያም ነገር እንደዛ ነው፡፡

ኢትዮጵያን ከመቃብር ማውጣት ባትችሉ እንኳን በእሷላይ እየተከመረ ካለው ድንጋይ፣ ድንጋዩን ባትችሉ፣ ጠጠሩን , ጠጠሩን ባትችሉ ከአፈሩም ቆንጥራችሁ ወዲያ በሉ፡፡ በቃ ስራችሁን ያዙ፡፡እነ እገሌን እነ እንትና እያሉ በሌላ ላይ ብቻ እጅ ማንሳት፣ ምላስ ማውጣት፣ ማውራት ይቁም፡፡አልአዛር ከሞት ይነሳል ብለው ድንጋይ እንዳነሱት እኛም በላያችን ላይ የተከመረው የባርነት ድንጋይ ይንከባለላል ብለን ለተግባር እንነሳ፡፡

ተማሪ ሆንክ ሰራተኛ በቤትህም የትም ሁን የት ፣ከመቃብሩ ላይ ካለው ነገር የቻልከውን አንሳ ከዛም የሁላችንም አልአዛር ይነሳል!!!!

አስብ---ወስን--አድርግ ከዛም ይሆናል!! ደግሞም ሃላፊነት መውሰድ እንማር!!
አባቶቻችን ሃላፊነት ወስደው አደርገዋለሁ ሞትም ቢሆን ምን አባቱ ብለው ለሀገራቸው ባይዋጉ ኖሮ ዛሬ በብዙዎቻችን ህይወትና ታሪክ ላይ እውነተኛ የባርነት ጠባሳ አፍጥጦ ይታይ ነበር፡፡
ያንን ጠባሳ ያጠፋው የነዛ አባቶቻችን ውሳኔና ተግባር ነው፡፡መቁረጥ!!
ይህ ለመፈጸም የሚከተሉት ጥቂት መንገዶች እንጠቀም
  • ·       የዘረኝነት እና የጎጠኝነት ፖለቲካ አስሽቀንጥረን በመጣል የህብረትና የአንድነት ስሜታችንን ማጠናከር
  • ·       የምእራባውያንን የኑሮ ዘይቤና ፍልስፍናን ወደጎን በማድረግ ኢትዮጵያዊ የሆነ የኑሮ ዘይቤያችንን እና ፍልስፍናዎች አጥብቆ  መያዝ
  • ·       እንደ አባቶቻችን እግዚአብሔርን በመፍራት ህይወት ውስጥ መመላለስ ናቸው፡፡