ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ርዕሰ ጳጳስ አቡነ ማትያስ ከየዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ ጋር
ሰላቢ እጆች የዲያብሎስ ዕቅድ አስፍጻሚዎች እንደመሆናቸው መጠን አንድ የዓለም መንግሥት ለመመስረት በሚደረገው ጉዞ የአለም ሃይማኖቶች ወደ አንድ ስርዓት
በመጠቅለል እውነተኛዋና ቀጥተኛዋ የተዋህዶ እምነት
ለማጥፋት የሚጠቀምበት አንዱ መንገድ ነው። የአለም ሃይማኖቶችን አንድ
ለማድረግ በሚያደርጉት ጉዞም የተለያዩ ማህበራትና ድርጅቶች በመመስረት የሃይማኖት ልማዶችና ተግባራት በመቀላቀል ዲያብሎሳዊ ዕቅዳቸው ለማስፈጸም ይሞክራሉ።ይህንን ተግባር መላው አለም የተዳረሰ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በቅድስት ሃገር ኢትዮጵያም መታየቱ አልቀረም።
ሰላቢ እጆች ይህንን ተግባራቸው ከሚፈጽሙባቸው ማህበራት አንዱ የኢትዮጵያ መጽሓፈ ቅዱስ ማህበር ነው።ይህ ማህበር የተለያዩ በክርስትና እምነት ሽፋን የተመሰረቱ ራሳቸው የእምነት ድርጅት ብለው የሚጠሩ ያቀፈ ነው።ታድያ እነዚ የእምነት ድርጅቶች የተለያየ የ አምልኮ
ስርዓትና ሕግ እያላቸው እንዴት በዚህ ማህበር አማካኝነት ሊስማሙ ቻሉ ፧ ብርሃንንና ጨለማስ እንዴት አንድ ላይ ሊታይ ይችላል ፧
ራስዋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ብላ የምትጠራ የግብፅ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተ ክርስትያን ቅርንጫፍ የዚህ ማህበር አባል ነች።ይህ ማህበር የሚያሳትማቸው መጽሐፍ ቅዱስም እውነተኛው ቃል የሻረና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለሚጥሩ ምዕራባውያን ያደላ ነው።በቅርቡ ይህ ማህበር ያሳተመው የትግርኛ ቋንቋ መጽሓፍ ቅዱስ እንኳን አንዱ ማረጋገጫ ነው።መጽሐፉ ተዋህዶን የማይወክልና በምንፍቅና የተጨማለቀ በመሆኑ የመቐለ ከተማ ምእመናን መጽሓፉ እንዳይሰራጭ ፌርማ በማሰባሰብ ለሚመለከተው አካል ጠይቀዋል።
በተመሳሳይ ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ጳጳስ አቡነ ማትያስ ከካቶሊክ ጋር ያለን ሃይማኖታዊ ልዩነት “ጠባብ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።የዲያብሎስ አገልጋይ ከሆነችው የቫቲካን ቤተ እምነት ግን ምንም የሚያገናኝን ነገር እንደሌለ የታወቅ ነው።ይህ ንግግርም ለዲያብሎስያዊ የኢሉሚናቲ እውነተኛዋንና ቀጣተኛዋን የተዋህዶ ሃይማኖት በአንድነት ሰበብ ስርዓትዋንና አምልኮትዋን ለማጥፋት የሚደረግ ዘዴ ነው።ይህንን ዜና የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን በህዋ ሰሌዳው የተደሰተበት በሚመስል መልኩ ለጥፎታል።
ዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ አየነው ቄስ ኦቭ ፌኪስ ቲቬትን ቅብአ ሜሮን ሲቀቡት
ከቀናት በፊት ይፋ የሆነው ምስል ደግሞ የሚያሳየን የኢሉሚናቲ መሠረታዊ ከሆኑት ቅርጾች መካከል እውነተኛዋን ተዋህዶ ሃይማኖት ለመበረዝና ለማጥፋት ከሚሰራው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ (World Councel of Churchs)አጠቃላይ ፀሃፊ በሰአሊተ ማርያም መቅደስ ውስጥ ከታቦቱና ከመሰዊያው ፊት ለፊት ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔር መቅደስ የሚያረክስ ተግባር ተፈጸመ።ይህ ተግባር የተፈጸመው የኦርቶዶክስ ካህን በሆኑት ዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ አየነው ከሃይማኖቱ እምነት ውጪ ለሆነው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ (World C)አጠቃላይ ፀሃፊና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ለሆነው ቄስ ኦቭ ፌኪስ ቲቬት (Rev.Dr
Olav Fykse Tveit) ቅብአ ሜሮን በመቀባት ተዋህዳዊ ክህነትን የረከሰበት ሁኔታ ነበር።ይህም ዋነኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ (WCC) የተመሰረተበት አላማ ነበር።
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ ምንድነው፧
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ መለያ ምልክት
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት መድረክ ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚመሰክሩት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር እና አዳኝ በመቀበል ለአንዱ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የጋራ ጥሪን ለመፈፀም የሚፈልግ የአብያተ ክርስትያን ስብስብ ነው።በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ፡ምዕመናዊ በመሆን አንድነት
እና አንድ የቅዱስ ቁርባን ኅብረት፣ በአምልኮ ውስጥ እና በክርስቶስ
የጋራ ሕይወት። ኢየሱስ ለተከታዮቹ እንደፀለየ ይህም ዓለም እንዲታመን እንደፀለየለት፣ ለዚህ አንድነት ወደ ፊት ለማደግ
ይፈልጋል።ይህም እውነተኛው ሃይማኖት ከክህደት ለመቀላቀልና ለመበረዝ ያስችለዋል።
በአለም ዙሪያ ከ 110 በላይ ሀገራት እና ግዛቶች ውስጥ ከ 500በ ላይ የሚሆኑ ክርስትያኖችን እና በርካታ የአለም ኦርቶዶክስ አብያተ፡ክርስቲያናት፣ የእንግሊዘኛ፣ የባፕቲስት፣ የሉተራን፣ የሜቶዲስት እና የተሃድሶ አብያተ፡ክርስቲያናትንም ጨምሮ፣ አብያተ፡ክርስቲያናትን፣ ቤተ እምነቶችን እና የቤተክርስቲያን ህብረትዎችን ያጠቃልላል።ብዙዎቹ አብያተ ክርስትያኖች የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ
ናቸው።ዛሬ አብዛኞቹ የአባል አብያተ፡ክርስቲያናት በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በካሪቢያን፣ በላቲን አሜሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በፓስፊክ
ይገኛሉ። አሁን 348 አባል የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት አሉ።
የዚህ ህብረት አባል አብያተ ክርስቲያናት፡
• በአንድ እምነት እና አንድ ቅዱስ ቁርባን ኅብረት ውስጥ የአንድነት ግብ አለው።
• ለሚስዮን እና ለወንጌል ሥራ ያላቸውን የተለመዱ ምስክርነታቸውን ያራምዳሉ።
• የሰዎችን ፍላጎቶች በማሟላት በክርስቲያናዊ አገልግሎት ውስጥ መሳተፍ፣ በሰዎች መካከል ያሉ እንቅፋቶችን በማጥፋት፣ ፍጥን እና ሰላምን በመሻት፣ እና የፍጥረትን ታማኝነት ከፍ ለማድረግ ይሰራሉ።
• በአንድነት መታደስ፣ አምልኮ፣ ተልዕኮ እና አገልግሎት ይፈጽማሉ።
ቄስ ኦቭ ፌኪስ ቲቬት ማነው ፧
ከላይ እንደተገለጸው ይህ ሰው በዶ/ር አባ ኃይለማርያም መለሰ አየነው ቅብአ ሜሮን በሰአሊተ ማርያም መቅደስ ውስጥ የተቀባ ነው።ቄስ ኦቭ ፌኪስ ቲቬት እ/ኤ/አ በነሐሴ ወር 2009 የዓለም
ዓቀፍ አብያተ፡ክርስቲያናት ጠቅላይ ጸሐፊ ሆኖ ተመርጧል። እ/ኤ/አ ሀምሌ 2014 ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠዋል። እ/ኤ/አ ከ
2002 – 2009 የኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን ስለ ጳጳሳት እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክር ቤት ጠቅላላ ጸሃፊ ሆኖው አገልግለዋል።
የዓለም ዓቀፍ አብያተ፡ክርስቲያናት ጠቅላይ ጸሐፊ ሆኖ ከመመረጡ በፊት በማህበሩ ውስጥ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእምነት እና የሥርዓተ፡ደህንነት
ኮሚሽን አባል በመሆን እና የፍልስጤም እስራኤል የእኩልነት መድረክ ማዕከላዊ ቡድን ተባባሪ ሆኖ አገልግሏል። በትውልድ ሃገሩ ኖርዌይ
ውስጥ የኖርዌይ ቤተክርስትያን አስተባባሪ፣ የኖርዌይ ኢስላማዊ ምክርቤት አማካሪ፣ የኖርዌይ ክርስቲያን ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
አባል በተጨማሪም የኖርዌይ የእምነት ግንኙነት ኮሚቴ አባል እና የኖርወይ ቤተክርስቲያኖች ባለአደራዎች ቦርድ አባል ነበር።
ቀደም ሲል በተሰጣቸው ስራዎች ከ 1999-2000 ለኖርዌይ ቤተ ክርስቲያን ፀሐፊነት የዶክትሪን ኮሚሽን እና ከ 2001-2002 የቤተ፡መንግስት ግንኙነት ሆኖ በመስራቱ በቀጣይ የፓስተርነት ማዕርግ ተሰጥቶታል።እ/ኤ/አ
በ 2002 በኖርዌይ የሥነ፡መለኮት ትምህርት ቤት በሃይማኖቶች አንድነት እንዲፈጠር በመስራቱ የዶክትሬት ማዕርግ ተሰጥቶታል።በአሁኑ
ወቅም የዓለም ዓቀፍ አብያተ፡ክርስቲያናት ጠቅላል ጸሓፊ ሆኖ ይሰራል።
የዓለም ዓቀፍ አብያተ፡ክርስቲያናት እንደገለጽኩት እውነተኛዋን የተዋህዶ ሃይማኖት ለማጥፋት የሚሰራ የኢሉሚናቲዎች መሳርያ ነው።ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እንደነገረን ሃይማኖት አንድ ነች እሷም ከአዳምና ሄዋን ጀምራ የነበረች ቀጥተኛዋ ዘላለማዊትዋ ተዋህዶ። ይህችን ለማጥፋት ዲያብሎስ የሚሸርበው ሴራ በጸሎትና በጾም ኢትዮጵያዊው እውነተኛው መንፈስ በመላበስ ልናሸንፈው እንችላለን።ዘመናዊነት ተገን በማድረግ ሁሉም ሃይማኖቶች ጠቃሚ ናቸው የሚለው ስጋዊ የዲያብሎስ ሽንገላ ሊያሸንፈን አይገባም።
‹‹እኔ በምድር ላይ ሰላምን ያመጣሁ ይመስላችኋል ፧ እኔስ ያመጣሁት መለያየትን እንጂ ሰላምን አይደለም እላችኋለሁ።››
---ሉቃስ ፲፪፡፶፪
‹‹እኔ የመጣሁት ወንድ ልጅን በ አባቱ ላይ ፥ ሴት ልጅን በእናትዋ ላይ ፥ ምራትን በዐማትዋ ላይ ፥ በጠላትነት ለማስነሣት ነው።››
---ማቴዎስ ፲፡፴፬
ለብዙ ዘመናት እውነት መስሎን የተቀበልናቸው ነገሮች በንጹህ ልቦና ልንመረምርም ይገባናል።ቤተክህነት(ሲኖዶስ) እንኳ በያዝነው ወር ባደረገው ስብሰባ ከ1600 ዘመን በኋላ “እኛ እዉነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነን፣ እንደራሴ ነን፣ ለኢትዮጵያም ተጠሪና መሪ ነን” ይሉ የነበሩት የግብፅ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሪዎች የነበሩት ፓትርያርክ፣ ጳጳሳትና መነኮሳት ኢትዮጵያዉያን የራሳቸዉን ፓትርያርክ፣ ጳጳስ እንዳይኖራቸዉ በአዋልድ መጻሕፍት ዉስጥ እንደ ዶግማ ያስቀመጡትን የተሳሳተ እንክርዳድ እዉቀት፤ የተሳሳተ እንደነበረና ከመጻሕፍት ዉስጥም እንዲወጣ መወሰኑ እንዲሁም በአንዳንድ አዋልድ መጻሐፍት ዉስጥ አንዳንድ ጎሳዎችና ማኅበረሰቦች በአሉታዊ መልክ እንዲገለጹ የተደረጉት ከቅድስት ቤተክርስቲያን አለመሆኑንና ግለሰቦች እንዳደረጉት በግልጽ ተገልጿል፡፡ ይህ የሚያሳየን እንደ ትክክል እንቆጥራቸዉ የነበሩ አንዳንድ እዉነታዎችና እዉቀቶች የተሳሳቱ ሆነዉ ሊገኙ እንደሚችሉ ነዉ፡፡
እግዚአብሔር ለሃይማኖት አባቶቻችንና ለእኛ ጽናቱ ይስጠን።
ግንቦት 8,2009 ዓመተ ምሕረት
No comments:
Post a Comment