EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 17 August 2017

ከአምልኮተ መለስ በስተጀርባ

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
አንደኛ - ይህ መልዕክት በሥጋና ደም ስሜታችን ለመረዳት መሞከር ለተጨማሪ የክህደትና ዓመፃ  ይዳርገናል።

ሁለተኛ - ስጋ የለበሰ ሰው የሰውን ሞት ሊያስደስተው አይገባም።ምክንያቱኢም እርሱም ይህንን ዓለም ተሰናብቶ መሄዱ አይቀሬ ነውና።ስለዚ ተከታዩ ጽሑፍ የተጻፈው በ አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ሞት በመደሰት የተጻፈ እንዳልሆነ መገንዘብ ጠቃሚ ነው።

ሦስተኛ - አቶ መለስ በቅዱስ ኩዳን ተዋህዶና ሃይማኖትና ኢትዮጵያ የፈጸሙት የክህደትና የዓመፃ ድርጊት የጨለማው ገዢ አገልጋይነታቸው ያረጋገጠባቸው ነው።ይህንን ደርጊታቸው በንስሃ እንዲተዉትና ወደ የእግዚአብሔር እውነት እንዲቀርቡ በቅዱስ ኩዳን ተዋህዶ ሃይማኖት የእግዚአብሔር አገልጋይ ተክለ ኪዳን መልዕክት ቢላክላቸዉም ዕድሉ ሳይጠቅሙበት በመቅረታቸው እግዚአብሔር ስራው ሰርታል።ይህንን የሚገነዘብ የጨለማው ገዢ ፖለቲከኞን፣ ካድሬዎችንና ጭፍን ሰዎችን በማታለል ሰማቸው በማግነንን አቶ መለስ ለዋሉለት ዉለታ በ አምልኮት እየከፈላቸው በመሆኑ ህዝቡ እንዲነቃና እሳቸውን ከማግነንና ከማምለት መቆጠብ ይገበዋል።




ተከታዮ  መልዕክት በኪዳናዊ ተክለ ኪዳን ከ ፭ ዓመት በፊት የተላለፈ ነው።

ጸሐፊዉ ኃዘንተኛና መከረኛ በሆነበት ዓመት በየካቲት27/2004 ዓ.ም በእግዚአብሔር አሳሳቢነት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ የተጻፈ የመጀመሪያ የደብዳቤ መልእክት፡
ቀን 27/06/2004 ዓ.ም
ለተከበሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ

በመጀመሪያ የንስሐ እድሜዉን ሰቶን እኔን መልእክት እንዳደርስ እርሶም እንዲደርሶት ፈቃዱ የሆነዉ እግዚአብሔር አምላክ ፈጣሪያችንን እያመሰገንኩ ወደ ዋናዉ ጉዳዬ እገባለሁ፡፡
ከየካቲት 20 እስከ 30/2004 ዓ.ም ድረስ የሕዳሴዉን ግድብ በተመለከተ ጥያቄና አስተያየት እንድንሰጥ በተከፈተልን ልዩ መገናኛ መስመር ይኸዉ እኔም እድሉን በመጠቀም ስለ ሕዳሴዉ ሆነ ስለ ወሳኝ ጉዳዮ አስተያየቴንና ጥያቄዬን እንደሚከተለዉ አቀርባለሁ፡፡
በመጀመሪያ ስለ ኢትዮጵያ ልማትና እድገት፣ ብልጽግና እንዲሁም ስለ ሕዝቡ መልካም ኑሮና ሕይወት የማያስብና የግሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ የማይነሳሳ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምናልባት ኢትዮጵያዊነቱን እንዲጠላና በዉስጡ ጥላቻ እንዲፈጠርበት ካልተደረገበት በስተቀር፡፡ ነገር ግን ለፓለቲካ መጠቀሚያ፣ ለራስ ስዉር ዓላማ ማሳኪያ፣ እንዲሁም ለሕሊና ማሸጫ ለሚሆን ቅስቀሳ ደግሞ “ከነፈሰዉ ጋር አንነፍስም፣ እንደ ቦይ ዉሃ ወደተፈለገዉ አቅጣጫ አንነዳም፣ሕሊናችንን አንሸጥም፣ ጥሩንባ አንነፋም፣ ቅድሚያ የሚሰጠዉ ስራ ሆነ ድርጊት በመጀመሪያ ትኩረትና ቅድሚያ ይሰጠዉ፤” የሚሉ ለሕሊናቸዉና ለአምላካቸዉ የታመኑ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉም ሊታወቅ ይገባል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለእናት አገራቸዉ እንኳን ገንዘባቸዉንና እዉቀታቸዉን ብቻ አይደለም ሕይወታቸዉን አሳልፈዉ የሚሰጡ እንደ ቀድሙት ቆራጥና ጀግና አባቶቻቸዉና እናቶቻቸዉ ለጊዜያዊ ሥልጣን ሆነ ጥቅማጥቅም እንዲሁም ክብርና ዝና ሲሉ ሕሊናቸዉን የማይገለባብጡና የማይሸጡ፤ ራሳቸዉን የካዱና ስለ እዉነትም የሚመሰክሩ፤ በዚህ ምክንያት የሚመጣባቸዉን ማንኛዉ ፈተናና መከራ በትእግሥትና በጽናት የሚወጡ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ፡፡
ስለ ሕዳሴዉ ግድብ ይህን ካልኩ ወደ ሁለተኛዉና ለእርሶም ሆነ ለዓለም ሕዝብ ወሳኝ ወደሆነዉ ጉዳይ እገባለሁ፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱ የአዳም ዘር በምሳሌዉ ሕያዊ ባሕርይ እንዲኖረዉና እርሱን የመምሰል ጸጋ ስለሰጠዉ ከእያንዳንዱ መልካም ፍሬ ይፈልጋል፡፡ በተለይ ብዙ ጸጋ ከተሰጣቸዉ ኢትዮጵያዉያን ብዙ መልካም ፍሬ የሚፈልግ ሲሆን፤ ነገር ግን እንኳን ብዙ ፍሬ ሊያገኝበት ቀርቶ መልካም ፍሬ የሚመስለዉን ለማጥፋት ነዉ ትዉልዱ ቆርጦ የተነሳዉና በዓመፃና በክህደት ሕይወት የጸናዉ፡፡ እርሶና መሰሎቾት ደግሞ በዋናነት ለጥፋቱ መሪና ተዋናይ ናችሁ፡፡ ለዚህም ዋጋ እንደምትከፍሉበት ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በፍርዱ አንዳች አድሎ የሌለዉና ለእያንዳንዱ ዓመፀኛና ከሃዲ እንደ ስራዉ በምድርም በሰማይም ዋጋ እንዲከፍልበት ያስደርገዋልና ነዉ፡፡ ምናልባት ዓመፀኛና ከሃዲ የሚለዉ ትርጉም በእናንተ ሐሳብና ተግባር በተቃራኒ የተሰለፈ ሰዉ እንዳይመስላችሁ፡፡ በእግዚአብሔር እዉነትና በቅዱሱ ኪዳን ላይ ያመፀ፣ የካደና አምልኮ ምንዝርና የፈጸመ ሰዉ ነዉ፡፡
እናንተ “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” የምትሉት ሆነ “የዓለም መንግሥታት መሪዎች ነን” የሚሉት ሰዎች፤ ሁላችሁም በአራቱም ማእዘን የዲያብሎስን ፈቃድ እየፈጸማችሁና እያስፈጸማችሁ በመሆኑ እጅግ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ በእግዚአብሔር ቁጣ ከወንበራችሁ በአንድም ይሁን በተለያየ መንገድ ትቆረጣላችሁ፡፡ ስለ ዓመፃችሁም ከእግዚአብሔር የከፋዉን ዋጋ በዚህ ምድር ዉስጥ እያላችሁ ትቀበላላችሁ፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጥሪ በተለያየ ጊዜ በእዉነተኛ ባለሟሎቹና እንደራሴዎቹ ቀርቦላችሁ ንቃችሁ በመተዋችሁና የእግዚአብሔርንም ደምፅ ለመስማት ፈቃደኛ ባለመሆናችሁ ነዉ፡፡ እግዚአብሔር ቃል በቃል የተናገራችሁንና የመጨረሻ ፍርደ አፈጻጸም ዉሳኔዉ ምን እንደሆነ ለማወቅ ከፈለጋችሁ በእኔ በተራዉና በደካማዉ፣ በመሃይሙና በኃጢአተኛዉ በኩል በመስከረም 2003 ዓ.ም “የኢትዮጵያና የዓለም የመጨረሻ ፍርድ አፈጻጸም ዉሳኔ” በሚል ርእስ ባስተላለፈዉ መልእክት በክፍል ሁለት በምእራፍ ሁለት በገጽ 32 በአንቀጽ 4 ላይ ለዓለም መንግሥታት የተናገረዉ ቃል “ታዲያ ይህን ሁሉ ስታደርጉ ዝም ብዬ የማያችሁ አይምሰላችሁ፤ እናንተ ለረጅም ጊዜ እንኖራለን፣ የራሳችን ሐሳብ እናጸናለን፣ ለትዉልዳችን እናስተላልፋለን ትላላችሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ሐሳባችሁ ይሻራል፤ ይቆረጣል፤ ፍሬ ሊያፈራ ለሚችል ይሰጣል፡፡” በማለት ነዉ፡፡
ለእናንተ “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” ለምትሉት ደግሞ፤ በክፍል ሦስት በገጽ 56 በአንቀጽ 2 “በቃ የእናንተም የዓመፃና የርኩሰት ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ነዉ፡፡ የዘራችሁትን የክፋት፣ የተንኮል፣ የዘረኝነት፣ የጥላቻ፣ የመለያየት፣ የክህደት፣ የርኩሰት ፍሬያችሁን ታጭዳላችሁ፡፡ ከወንበራችሁ ትቆረጣላችሁ፡፡ በቅንነትና በእዉነት ለሚመላለሱ፣ የእኔን ፈቃድ ለሚፈጽሙና ለሚያስፈጽሙ ለድንግል ማርያም ምርጥ ባለሟሎች ሥጋዊዉንም መንፈሳዊዉን ወንበር አሳልፌ እሰጣለሁ፡፡ የጽድቅ ፍሬ ያፈሩበታል፡፡ በርኃብ፣ በችግር፣ በልመና፣ በጦርነት፣ በጉስቁልና፣ በዓለም ዘንድ እንድትታወቅ ያደረጋችኋትን “ ሀገረ እግዚአብሔር” የተባለች ምሥጢር አገሬ የቅድስት ድንግል ማርያም አስራት አገር የቀደመ ክብሯ ይመለሳል፡፡ ከራሷ አልፋ ለዓለም ብርሃን ትሆናለች፡፡ ልጆቿን በአራቱም ማእዘን ትሾማለች፡፡ በጎቼን በመልካም ሕይወት እንዲኖሩ ታደርጋለች፡፡” በማለት ነዉ የተናገረዉ፡፡
ታዲያ ይህን የተናገረዉን የሚያስቀር ሃይል በዓለም ላይ ያለ ይመስሎታል? ምናልባት ነጥብ በማትሞላ እዉቀቱና ጥበቡ እንዲሁም ከልምሾነት በማያልፈዉ ኃይሉ የሚመካ፣ የቅርፊት ሥጋዉ ስሜት ያየለበት ሰዉ፤ “ ይህማ በምንም ዓይነት ሊሆን አይችልም” ሊል ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር እዉነታ እግዚአብሔር የተናገረዉን የተባበሩት መንግሥታት ሆነ የአዉሮፓ ሕብረት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት በአንድላይ ቢሰለፉ ሊያስቀሩ አይደለም አንድ ቀን የማዘግየት አቅምና ኃይል የላቸዉም፡፡ ምክንያቱም እንኳን በግዙፉ አካል የተገለጹት ሰዎች ቀርቶ በረቂቅ አካል የተገለጹት ሰይጣናት አንድነትና ሕብረት ፈጥረዉ የእግዚአብሔርን ስራ ለማስቀረትና ለማዘግየት ቢሞክሩ አይቀጡ ቅጣት ተቀተዉና ዋጋ ከፍለዉበት ያልፋሉ ፍዳቸዉን ይቀበላሉ እንጂ፤ በየትኛዉም ቦታ ማንኛዉም ፍጡር እግዚአብሔርን ማሸነፍ ቀርቶ ሊገዳደረዉ የሚችል የለም፡፡ ስለዚህ የዓለም መንግሥታት ሆኑ፤ “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” የምትሉትና በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የምታላግጡት ሁሉ! የሚያዋጣችሁ ካለምንም ቅድሜ ሁኔታና ድርድር እጃችሁን ለእግዚአብሔር መስጠትና ወንበሩንም በእርሱ ለተመረጡትና ለተቀቡት ለኢትዮጵያዉያኑ ርእሰ ነገሥታት(ንጉሠነገሥት)ና ለካህኑ እጨጌ አሳልፋችሁ በመስጠት በእዉነተኛ ንስሐ በእግዚአብሔር ሥርዓት ዉስጥ መመላለስ ብቻ ነዉ፡፡
የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር! ስለዚህ ለልማቱም ሆነ ለጥፋቱ እንዲሁም ለዓመፃና ክህደት ተግባር ከዓለም መንግሥታት ጋር አንድነት ፈጥረዉ እንደተሰለፉ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ ፈቃዶት ከሆነ ነፍሳትን ለማዳን (የዓለም ሕዝብ ከጥፋትና ከጠረጋዉ ለመታደግ) ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ የሆኑት 76 ገጽ የመጀመሪያዉን የእግዚአብሔር መልእክት፣ 463 ገጽ ሁለተኛዉን መልእክት እንዲሁም የመጀመሪያዉንና ሁለተኛዉን ደብዳቤ ለዓለም መንግሥታትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በይፋ እንዲያቀርቡ በትህትና እጠይቃለሁ፤ አሳስቦታለሁ፡፡ ይላል ታናሹ ወንድሞት፡፡
ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ማርያም ፡፡
እግዚአብሔር ቅዱስ ኪዳኗን ኢትዮጵያን ይባርክ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅ
ከእግዚአብሔር ባሪያ አንዱ
ግልባጭ
፦ለእዉነተኛዉ ለእግዚአብሔርና እመቤታችን ድንግል ማርያም ባለሟልና እንደራሴ ኢትዮጵያዊዉ እጨጌ
፦ለእዉነተኛዉ ለእግዚአብሔርና እመቤታችን ድንግል ማርያም ባለሟልና እንደራሴ ኢትዮጵያዊዉ ርእሰ ነገሥታት(ንጉሠ ነገሥት) ኢትዮጵያ በመጀመሪያዉ፣በሁለተኛው፣ በሦስተኛዉ ዙር በኢሜልአድራሻችሁ የእግዚአብሔር መልእክት ለተላከላችሁ ሁሉ ባላችሁበት በአንድነትና በሦስትነት ለሚመለከዉ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላካ ማሳሰቢያ አሁን ለምታነቡት  የመጀመሪያዉና ሁለተኛዉ የእግዚአብሔር መልእክት ገጻቸዉ የሚገልጸዉ ቀደም ሲል ከመታተማቸዉ በፊት በሶፍት ኮፒ ባላቸዉ ገጽ ብዛት ሲሆን አሁን ከታተመዉ ጋር ክፍሉና ምዕራፉ አንድ አይነት ነዉ ገጽ ቁጥሩ ብቻ ነዉ የሚለያየዉ፡፡




No comments: