ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ውድ ኢትዮጵያውያንና ለእውነት የቆማቹ የሰው ልጆች በጠቅላላ ጊዜው በከፍተኛ ደረጃ መንፈሳዊ ጦርነት የሚካሐድበት ወቅት መሆኑ አትክዱትም።ራሳቸውን የአምልኮ መልክ ያላቸው በማስመሰል የክህደትና የዓመጻ ድርጊታቸው የሚፈጽሙ የባቢሎን ቅሪት የሆኑት የሓሰት እምነት ድርጅቶች መልካቸው በመቀያየር የሰው ልጅን በጠቅላላ ለዲያብሎስ ለማስገዛት የሚያደርጉት ጉዞ እግዚአብሔር እውነት እንዲገልጡ ባቆማቸው ሰዎች የሰይጣን አምልኮ ገመናቸው እየገለጠላቸው መጥቷል።እውነት ብቻ ለሚፈልግ ሰው ይህንን ሁኔታ ለመረዳት አያስቸግሮዉም።
የሰላቢ እጆች (ኢሉሚናቲ) የሓሰት እምነት (ሃይማኖት ለማለት አልችልም ምክንያቱም ሃይማኖት አንዲት ናት) መፈልፈያ መሳርያ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ነች።ከዚች የእምነት ተቋም ተሃድሶን ያስፈልጋል በማለት ከ500 አመታት በፊት በመገንጠል የራሱ የግሉ የሆኖውን እምነት በመያዝ ነበር ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር የፕሮቴስታንት የምንፍቅና እምነት የመሰረተው።
የፕሮቴስታንት የምንፍቅና እምነት የተመሰረተበት 500ኛው አመት ለማክበር በመላው አለም ያሉ የእምነቱ ተከታዮች ከሃገረ ጀርመን ጀምሮ በመላው አለም ለማክበር በዝግጅት ላይ ናቸው።ይህንን ተከትሎ አንድ የፕሮቴስታን ሰነ መሎኮት ምሁር http://religionnews.coma በተሰኝ የህዋ ሰሌዳ (website) በታተመ ጽሑፋቸው ማርቲን ሉተር የፕሮቴስትንት የምንፍቅና እምነት ሲመሰርት ኢትዮጵያ የክህደት እምነቱ ለማስፋፋት ዋነኛና ቀዳሚዋ ዕቅዱ እንደነበረች በግልጽ ገልጸዋል።
ይህ ዲያብሎስ ከጥንት ጀምሮ ዋነኛዋ የጥቃትና የሴራ መዳረሻው ኢትዮጵያ መሆንዋ ለተገነዘበ ሰው አዲስ መረጃ አይደለም።ዲያብሎስ እውነተኛ ፣ ቀጥተኛና ህያው
የሆነው የቅዱስ ኪዳን ተዋህዶ ሃይማኖት ከ7510 አመታት በፊት ተቀብላ አጽንታ የያዘቺው ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ስለሚያውቅ የጥፋት ሃይሉም በዚች ምድር ይበረታል።ይህ ጸረ ጌታችንና መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የሆነው ሓሳዊ ክርስቶስ ነኝ ባይ መንፈስ በዘመኑ ድህነታችንና ቅዱስ ኪዳን ተዋህዶ እምነትን ባለማወቃችን ምክንያት በማድረግ ዜጎቻችንን ለመንፈስ ድህነትና ጉዳት እየደረገ ነው።
በየጸበሉ ሓሳዊ ክርስቶስ መሆኑ ራሱን የሚያጋልጠው ይህ የወደቀ መንፈስ ተሃድሶ በሚል አጉል ምክንያት ቅዱስ ኪዳን ተዋህዶ ሃይማኖትን ለመበረዝና ኢትዮጵያዊያን ለዲያብሎስ ለማስገዛት የሚያደርገው ትግልም በተለያዩ መንገዶች እየሰማንና እያየን ነው።በመጨረሻ በዚህ የክህደትና ዓመጻ ሃይማኖትና አምልኮ መሳይ ስይጥንና ያላቹ የቅድስት ምድር ኢትዮጵያ ልጆች ወደ ቀጥተኛዋና ዘላለማዊትዋ ቅዱስ ኪዳን ተዋህዶ ሃይማኖት እንድትመለሱ ወንድማዊ ምክራችን እንለግሳለን።
ሰኞ ጥቅምት 20, 2010 ዓመተ ምሕረት

No comments:
Post a Comment