EAR

አዲስ ነገር

Friday, 3 November 2017

ኢትዮጵያና ህወሓት

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


Red Flag Attack "የማስጠንቀቅያ ጥቃት ምልክት" በሚል ሊተረጎም ይችላል። የሴራ ተመራማሪዎች በብዛት የሚጠቀሙበት ቃል ነው።የቃሉ ፍቺም የሚከተለው ነው አንድ ለማስፈጸም የምትፈልገው አላማ ወይም ዕቅድ ካለ ሌላ አካል  በመጠቀም  እንዲፈጽመው ወይም እንደፈጸመው በማስመሰል በማላከክ ከችግሩ አላማን ማሳካት መቻል ነው።ይህ ዘዴ የሚጠቀሙት ምዕራባውያን የምስጥር ማህበረሰቦች ናቸው።

ዘዴው ምሳሌዎች በመጥቀስ እንመልከተው።ከቀናት በፊት የአሜሪካው ርዕሰ ሥልጣን ባለቤት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ሎቶሪ እንደሚያቆሙ ሲናገሩ ነበር።ምክንያቱም ዲቪ ሎቶሪ (Diversity Visa) ደርሶት ወደ ሃገረ አሜሪካ በገባ የውጭ ዜጋ በመኪና ማሽከርከር ኒውዮርክ ከተማ ላይ የሽብር አደጋ ስላደረሰ የሚል ነው።ይህ ትራምፕ ሓሳብ ማመን ጅልነት ነው።አሜሪካ ዲቪ ሎተሪ የምትሰጠው  ለውጭ ዜጎች በማሰብ ከመሰለን ተሳስተናል።አባቶቻችን የናቁት ባርነት በረቀቀ ዘዴና የኛ በጎ ፍቃደኝነት ተጨምሮበት ለማስፈጸም እንጂ።በኒውዮርክ የደረሰው የሽብር ድርጊትም ሆን ተብሎ በአሜሪካው የሰለላ ድርጅት (CIA) የተቀነባበረ ነበር።የሽብር ድርጊቱ እንዲፈጸም በማድረግ ትራምፕም በዚ ድርጊት የተቆጡ በማስመሰል የዲቪ ሎቶሪ እንደቆመ በመግለጽ ይህንን ሎቶሪ ሲጠባበቁ የነበሩት ርካሽ ጉልበት ለአሜሪካ ሊሰጡ የሚችሉ ኢትዮጵያዊያናን ሌሎች ዜጎች የሚሰጡት ምላሽ በማጥናት ዘመናዊ ባርነቱ አሜሪካ በምትፈልገው መንገድ ሊቀጥል ይችላል ወይም አይችልም ለሚለው ጭንቀታቸው ማረጋገጫ ለማግኝት ነው።ርካሽ የሰው ጉልበት የአሜሪካ የሰነ ቁጠባ (Economy) መሰረት ነውና።ትራምፕ የዲቪ ሎቶሪ ሊያቆም ይችላል ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል።

ሁለተኛው ምሳሌ 2001 እ/ጎ/አ በሃገረ አሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በአለም ንግድ ድርጅት ህንጻዎች ላይ የደረሰው የሽብር አደጋ በጊዜው ርዕሰ ስልጣን ባለቤት ጆርጅ ቡሽና ኤፍ..አይ የተቀነባበረ ቢሆንም አሜሪካ በተቆጣጠረቻቸው የዜና አውታሮች የእስልምና ሃይማኖት ሽፋን በማድረግ በቢን ላደን በሚመራው አልቃይዳ የሽብር ቡድን እንደተፈጸመ አውጃለች።ይህም እስልምና ሃይማኖት የሽብር ሃይማኖት ነው የሚል ሃሳብ እንዲሰርጽ አድርጓል።የሚገርመው ነገር ቢን ላደን የሲአይኤ ባልደረባ የነበረ መሆኑ ነው።አሜሪካ አልቃይዳ የሚባል ራስዋ ያደራጀችው ቡድን ለማደን በሚል ሽፋን በተለያዩ የአረብ ሃገራት የሚገኝ የነዳጅ ዘይት ለመመዝበር ችላለች።ቢን ላደንም እንደ የሲአይኤ አባልነቱ ባራክ ኦባማ ገደልኩት እንደሚለው ሳይሆን በጤና እክል ምክንያት ቀድሞ ሞቶ ነበር።

ጆርጅ ቡሽ በጊዜው በሳዳም ሁሴን የምትመራው ሃገረ ኢራቅ አለምን ሊያጠፋ የሚችል የጋዝ ጦር መሳርያ ታጥቋል በሚል የውሸት ምክንያት አለም ህዝብ በማታለል ኢራቅን በመውረር እንዳልነበረች አድርጓታል።እስከ አሁንም ሰላም እንደናፈቀች ነች።በተቃራኒው ጆርጅ ቡሽ የኢራቅን ነዳጅ ፈልጎ ነበርና የወረራት ከስልጣኒ ሲለቅ የቡሽ ቤተሰብ የሃብት መጠን ስምንት እጥፍ ጨምሯል።ይህ ሰይጣናዊ ዘዴ በመጠቀም ነው እንግዲ ሰላቢ እጆች (ኢሉሚናቲ) የአለምን ህዝብ የሚያሸብሩት።ራሳቸው አሸባሪ ሆኖው ሳለ ሌሎች ንጹሃንን በአሸባሪነት የሚከሱት የሚያሳቁቁት።

ወደ ሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ስንመጣም ከአርባ ሥስት አመታት ጀምሮ የምዕራባውያንን ተላላኪ በመሆን የእግዚአብሔር የሆነዉን ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚሰራው ህወሓት የሚጠቀምበት ዘዴም ተመሣሣይ ነው።ይህም የድርጅቱ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በመጠቀም የሚሰራው ነው።ህወሓት ሲመሰረት ካቀዳቸው ነገሮች አንዱ ትግራይን መገንጣል የሚል ነበር።ይህ ምኞትም የተዳፈነ ቢመስልም በተለያየ ጊዜ በሚከሰቱ ነገሮች ይገለጣል።ይህንን ለማስፈጸም የሚሰሩ የድርጅቱ ካድሬዎ አሉ።አብዛኛው ደጋፊ ግን ይህንን ህቡዕ የሚመስል በረቀቀ ዘዴ ለመተግበር የሚደረግ መሆኑ አልተገነዘበም።መጀመርያ በተለያዩ የፈጠራ ታሪኮችና ወሬዎች ከእየአንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነት እንዲወጣና በብሔር እንዲተካ በየዋሁ ህዝብ ላይ ተሰርቷል።በነቀምት የተፈጠረው አሳዛኝ ሁኔታም በህወሓት የተቀነባበረ መሆኑ ግልጽ ነው።የዋሁ ህዝብ ግን በብሔር ጎራ ለይቶ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ሳይቀር ሳይገባው ህወሓት ባዘጋጀችው ወጥመድ ሥር ወድቋል።በማህበራዊ ትስስር የህዋ ሰሌዳዎች የምናየው የሁለቱም ጎራ በማወቅም ባለማወቅም  የሚያደርጉት የሚጽፉት ነገር ህወሓትን ለያዘችው አጀንዳ የሚጠቅማት ነው።በእውነት ኢትዮጵያውያን መሆናችን የምናምን ሰዎች ይህንን መገንዘብ ይገባናል።ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለማጥፋት የሚነሱ አካላት መቼም ቢሆን ተሳክቶላቸው አያውቅምና የሚያስፈራን ነገር ሊኖር አይገባል።ኢትዮጵያ በሰዎች ተንኮል የምትጠፋ አይደለችም።ጥፋትዋ የሚመኙ ግን ቀድመው ይጠፋሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ዋናው ሓሳብ ካልታተመው "ሰላቢ እጆች" መጽሐፍ የተወሰደ

ሓሙስ ጥቅምት 23, 2010 ዓመተ ምሕረት 

No comments: