EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 15 October 2017

ጽዮናዊነት በአግአዝያዊነት ሽፋን ኢትዩጵያዊነትን ለማጥፋት ሲጣጣር




ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

በተስፋጽዮን ፊትአውራሪነት እየተመራ ያለው የአግአዝያን እንቅስቃሴ ዛሬ በሃገረ እስራኤል እውቅና አግኝቷል።የአግአዝያን እንቅስቃሴ አቀንቃኞች በደመነፍስ በመመራት የሚሄዱበት መንገድ የገባቸው አይመስልም።ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ነገር መነሻ መሆኑ በመዘንጋት በተጠላለፈ ሴራ በ ፲፱ ክፍለ ዘመን በተመሰረተችው አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይሁዳውያን ነን በሚሉ አስመሳይ የኢሉሚናቲ አገልጋዮች ለሴራ ማስፈጸምያ በተመሰረተችው እስራኤል ቡራኬ እንዲሰጣቸው መፈለጋቸው አምጣ የወለደችውን እናቱን ትቶ ሌላ እናት እንደሚፈልግ ልጅ ይመስላሉ።አለማወቃቸው እንጂ ኢትዮጵያ አለሙ ለመዳን በመሮጥ የሚፈልጋት ባለ ጊዜ ነች።እንኳን በህወሓትና ሻዕብያ የተነጠለችው የኢትዮጵያ ክፍል የሆነችው ኤርትራን አይደለም እስራኤልን ጨምሮ መላው አለም ለመምራት የተመረጠች የእግዚአብሔር መንግሥት ነች።ታድያ ያልታደሉት እነዚህ የአግአዝያን እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ጽዮናውያን ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚያደርጉት ጥረት በማወቅም ባለማወቅም እየደገፉት መሆኑ ማወቅና ለሚመጣው የእግዚአብሔር ፍርድ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።ግንድ ከሆነው ኢትዩጵያዊነት የተነጠለው ቅርንጫፉ ኤርትራ ከግንዱ የሚያስፈልገው ንጥረ ነገሮች በማጣት ወደ በድንነት እየተቀየረ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው።

ሃገረ እስራኤል የሃገረ አሜሪካ ሞግዚትና የበላይ አዛዥ ነች።ዳግማዊትዋ ባቢሎን አሜሪካ ለምትፈጽማቸው የእጃዙር ሽበራዎች ዋነኛዋ ጠንሳሽ እስራኤል ነች።ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንን ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ድርጊቶች በመፈጸም የሰው ህይወት እየቀጠፈ ያለው የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ ቡድን በእስራኤል መሪነትና በአሜሪካ ድጋፍ እስልምና ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የአለም ህዝብ ለማሸበርና አቅጣጫ ለማስቅየር የተመሰረት ቡድን ነው።

አይ.ኤስ.አይ.ኤስ (ISIS) የሽብር ቡድን በፈረንሳይ እንግሊዝ ቤልጄምና የተለያዩ ሃገራት ሽብር ሲፈጽም አይ.ኤስ.አይ.ኤስ (ISIS) ከመሸገበት ቦታ በቅርብ ርቀት በምትገኝ ሃገረ እስራኤል (የክርስትና ቦታ የሆነች)  አንድ ጊዜ እንኳን የሽብር ተግባሩ አለመፈጸሙ ለምን ይሆን ፧ መልሱ ውሻ አሳዳጊውን አይናከስም የሚል ይሆናል።በተጨማሪ እስራኤል ባላት ሰይጣንዊ የስለላ መዋቅር በመጠቀም ማለትም ሞሳድ በተባለው የስለላ ድርጅትዋ የፍልስጤም ህዝብ በየቀኑ የምትገድልና ህጻንትን የምታሰቃይ  የኢሉሚናቲዎች አገልጋይ ነች።ጥንታውያኑ እስራኤላውያን ቢሆኑም መሰረታቸው ኢትዮጵያ ነበረች።በራዕይ ዩሓንስ እንደተገለጸው የአሁኖቹ እስራኤላውያን ግን አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉ ናቸው።

ስለዚ የአግአዝያን እንቅስቃሴ አራማጆችና ደጋፊዎች ቀደምትና ህያው በሆነው ኢትዮጵያዊ ማንነት በመጣበቅ የኢትጵያዊነት በረከት ተካፋይ እንድጦኑ እንጋብዛለን።በመቀጠል እንዴት ኢትዮጵያዊነት ከአይሁድነት በፊት የነበረና ለወደፊትም በእግዚአብሔር ተጠብቆ እንደሚኖር ለማስረዳት እንሞክራለን።

ኢትዮጵያዊው ትውልድ የአዳምና የሔዋንን ፍጥረት መነሻው አድርጎ የ፯ሽ፭፻፲ (ሰባት ሽህ አምስት መቶ አሥር) ዓመታት የነጻነት ህልውናን የሚያስቆጥረውን፥ በኢትዮጵያዊነቱም የሚያኮራውን ገናና ዝና ትቶ ዘወትር ሲለፍፍ የሚደመጠው የኦሪታውያኑ እስራኤሎች የተፅዕኖ ኃይል የኋላ ኋላ ወደኢትዮጵያ ገብቶ መስፈን የጀመረበትን ዜና መዋዕል ነው። ይኸውም እስራኤላዊው የተፅዕኖ ኃይል ከኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ማክዳና ከእስራኤላዊው ንጉሥ ሰሎሞን የተወለደውን የቀዳማዊ ምኒልክን የንግሥና ዘመን መነሻው ያደረገውን፥ አገዛዙንም፡ በዚህ መልክ፡ በራሱ፡ በኢትዮጵያዊው ትውልድ ላይ ሊያሰፍን ያስቻለውን ኢትዮጵያዊዉን የህልውና ዕድሜ በሦስት ሺህ ዓመታት ብቻ ወስኖ ይህን የስሕተት ዘመን ለመመሥረት የተጠቀመበት የሓሰት ይትበሃሉ መኾኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያዊው ትውልድ እስከዛሬና ዛሬም ያለኀፍረትና ያለይሉኝታ መላልሶ የሚናገረውና የሚጽፈው፥ የሚያሠራጨውና የሚያውጀው ይህ አሳፋሪ ይትበሃል በቤተ ሕዝቡ ዘንድ ቋሚ ባህል ኾኖ መቀጠሉ ብቻ ሳይኾን፥ የቤተ መንግሥቱ ሕጋዊ የአዋጅ ቃል፥ የቤተ ክህነቱም ሃይማኖታዊ አቋም ኾኖ የሦስት ሺሆችን ዓመታት ዕድሜን ማስቆጠሩ ይኸው እስካኹን ጸንቶ በቀጠለው የትውልዱ አመራርና አሠራር በጉልህ ይታያል።
ይኹን እንጂ እንኳንስ ኋላ በተከታታይነት ለመጡት ለኪዳነ ኦሪቱና ለክርስትናው የኪዳነ ምሕረት እምነቶች ቀርቶ ለመጀመሪያውና ለጥንታዊው የኪዳነ ልቦናው የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት ሃይማኖትም ጭምር፡ ምንጭ በኾነችው በኢትዮጵያ ይኸው ስሑት ይትበሃል ለዚህን ያህል ዘመን እንዲህ ተንሠራፍቶ ለመቀጠል መቻሉ ሳያስደንቅ አልቀረም። ማስደነቁም ያለምክንያት አይደለም፤ ይትበሃሉ የተሳሳተ መኾኑን አረጋግጠው የሚያስረዱ እንደዐለት የጸኑ የምስክር ሓውልቶች እያሉ ሓሰቱ ተጠናክሮ እስከዛሬ መቀጠሉ ነው፤ ከእነዚህ የምስክር ሓውልቶች መካከል ጥቂቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ተጠቅሰው ይገኛሉ፦ በቅድሚያ የዕብራውያን አባት የኾነውንና ጣዖት አምላኪ የነበረውን አብርሃምን ለኪዳነ ልቦናው የኢትዮጵያዊነት ሃይማኖትና በቅዱሱ ኪዳን አራተኛውን ተራ ለያዘው ለግርዛቱ ቃል ኪዳን ያበቃው ከአዳምና ሔዋን እስከኖኅ የደረሰውን የቅዱሱን ኪዳን ኢትዮጵያዊነት ሕያው ቅርስ የተረከበው ኢትዮጵያዊው መልከ ጼዴቅ መኾኑ ነው፤ (ዘፍጥ. ፲፬፥ ፲፰-፳። መዝ. ፻፱፥ ፬። የሓዋ. ፰፥ ፳፮-፴፱። ዕብ. ፯፥ -፳፰።

በመካከሉ እነዚህኑ "የአብርሃም ልጆች ነን!" የሚሉትን ዕብራውያንን ከግብፅ የባርነት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ለኪዳነ ኦሪቱ ሃይማኖትና ለከነዓን ምድረ ርስት ያበቃቸውን ሙሴን እግዚአብሔር አስቀድሞ ወደኢትዮጵያ አምጥቶ ስለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት እንዲያውቅና እንዲያምን፥ ኢትዮጵያዊቷን ሲጳራንም በሚስትነት እንዲያገባና ከእርሷ ልጆችን እንዲወልድ ካደረገው በኋላ በዚህ የኢትዮጵያዊነት ማንነቱ ወደፈርዖን መላኩ ነው፤ (ዘጸአ. - እና ፲፰፤ ዘኍል. ፲፪።

በመጨረሻ ከኢትዮጵያዊቷ የአምላክ እናት ከድንግል ማርያም ተወልዶ ፍጥረተ-ዓለሙን ያዳነው ኢትዮጵያዊው ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለተመሳሳይ ተልእኮ ከእርሱ እንደቀደሙት እንደመልከ ጼዴቅና እንደሙሴ "ኢተፈነውኩ ዘእንበለ ኀበ አባግዕ ዘተሓጕላ ዘቤተ እስራኤል!" ማለትም "የእስራኤል ወገን ወደኾኑ የጠፉት በጎች ካልኾነ በቀር፡ ወደሌላ አልተላክሁም!" ደግሞም "ወኢትፍትሑ፡ በአድልዎ ለገጽ! አላ ፍትሓ ጽድቅ ፍትሑ!" ማለትም "የእውነት ፍርድ ፍረዱ እንጂ መልክ አይታችሁ አትፍረዱ!" ብሎ ተናግሮ እያስተማረ በመስቀል ተሠውቶና ሞቶ እነዚህኑ ዕብራውያንን ያዳነው በዚሁ ኢትዮጵያዊነቱና መልኩ መኾኑ ነው። (ማቴ. ፲፭፥ ፳፬። ዮሓ. ፯፥ ፳፬።)

እሁድ ጥቅምት 5, 2010 ዓመት ምሕረት

No comments: