EAR

አዲስ ነገር

Friday, 10 November 2017

ፆታዊ እኩልነት በመጽሐፍ ቅዱስ


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

እግዚአብሔር ያለ ምክንያት የፈጠረው ፍጥረት የለምና ፍጥረቱን በእኩል ዓይን የሚመለከት ድንቅ አምላክ ነው።ስልጣኔ በሚል ሽፋን የሚንቀሳቀሱ የርዕዮተ ዓለም አራማጆች በየጊዜው በሚያነሱት ሓሳብ ወንድና ሴት እኩል መታየት አለባቸው የሚል አጀንዳ ያነሳሉ።ወንድም ሴትም የእግዚአብሔር ፍጥረት በመሆናቸው ድሮውንም እኩል ናቸው እንጂ አይበላለጡም።መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር እኩልነት የሚለው ጽንሰ ሓሳብ ያሚያራምዱ ሰዎች እኩልነት የሚገልጹበትና የሚያዩበት መንገድ ነው።
ይህ በአለማውያና ሰዎች የሚነሳው የሴቶች እኩልነት (feminism) ግን በአብዛኛው ጊዜ እውነታን የለቀቀና የእኩልነት ትርጉም የሚያዛባ ነው።ይህም ሆን ተብሎ ላይ ላዩን ማር በሚመስል ንግግር እግዚአብሔር የፈጠረውን ተፈጥሮ መቃረንና መቃወም ነው።

ወንድና ሴተ በተፈጥራቸው እኩል ሲሆኑ በተሰጣቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ግን የሚለያዩባቸው ነገሮች አሉ። ይህንን ደግሞ በሰውኛ መንገድ ወይም ፍልስፍና መጣስ አይቻልም።

ካርል ማርክስ የኮሚኒዝም ርዕየተ ዓለም ሲያብራራ ቤተሰብ የሚባል ተቋም ፈርሶ ልጆች በመንግሥት ሥር ማደግ አለባቸው ይላል።ይህም ውስጠ ሚስጥሩ ቤተሰብ በማስፍረስ ተፈጥራዊው የሆነው ሰነተዋልዶ በማጥፋት ኢ-ተፈጥራዊ የሆነው ግብረሰዶማዊነትና ሌሎች ሰይጣናዊ ድርጊቶችን ማህበረሰቡ ማለማመድ ያለመ ሴራ ነው።

የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ የሁሉም ጥያቄዎች መልስ የሚገኝበት መጽሐልፍ እንደሆነ የኔ እምነት ነው።በዚ መሠረት ስለ ባልና ሚስት (ወንድና ሴት) ምን እንደሚል የተወሰኑ የአዲስ ኪዳን ቃላት እንመልከት።

ቆሮንቶስ ፩፩፥ ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። የሴትም ራስ ወንድ ነው፤ የክርስቶስ ራስ ደግሞ አምላክ ነው።

ቆሮንቶስ ፩፩፥ ፰ -፲ ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። ሴት ግን የወንድ ልጅ ናት። ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና። ሴት ግን ለወንድ ልጅ ታገኛለች። ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል።

ጢሞቴዎስ ፪፥ ፩፩ - ፩፬ ቀና ሴት ሁሉን ይገዛ ዘንድ ዝም ይበሉ። ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፣ ከዚያም ሔዋን። የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤

ቲቶ ፪፥ ፩፡፭ - አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር። ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው።

ኤፌሶን ፭፥ ፪፪፡፫፫ ሚስቶች ሆይ፥ ጌቶች ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና። ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።

ኤፌሶን ፭፥ ፩፮፡፩፰ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ ቆመ፥ እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደ ገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል። የገዛ ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል፤ ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ታላቅ ምሥጢር ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ። ሚስቱም ባሏን እንደምታከብረው ይገነዘባል።

ጥቅምት 10, 2006 ዓመተ ምሕረት

No comments: