ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ሳይንስ የሚለው ቃል ከላቲን scientia (ስኪየንቲያ) የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ዕውቀት” ማለት ነው። ዕውቀት
ጠቃሚ ብቻ ነው በሚል ትርጉም ሁሉም ዕውቀት ግን ሳይንስ ሊሆን የሚችል
አይመስለኝም። የአሁኑ ጊዜ አለማችን በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ከፍተኛ የስልጣኔ ደረጃ እንደደረሰች አብዛኛው ሰው የሚስማማበት ይመሥላል።የአዳም እግር አሻራ ባለባት ሃገረ ኢትዮጵያ ግን አለም አሁን ላለችበት ስልጣኔ መሠረት የሆኑ ጥበቦች ነበርዋት አሁንም አሏት።
አሁን ምዕራባውያን በተቆጣጠሩት ሳይንስ የሴራና የክህደት ማስፈጸምያ ሆኖ የአለም ፍጻሜ እያፋጠነው መጥቷል።እኛ ግን የአባቶቻችንን ቅዱስ የሆነውን ጥበብ በመለያት ልንጠቀምበትና የመንፈስ የበላይነታችንን ማስመስከር አለብን።
ናሳ (NASA) የተባለው የውሸት መረጃ አሰራጭ ከመመሠረቱና ስራ ከመጀመሩ በሺዎች ከሚቆጠሩ አመታት በፊት “አሀመነስ“ የተባለ ኢትዮጵያዊ ህዋ ላይ ፲፮ ፕላኔቶች እንዳሉ መዝግቦ ነበር።አሁን ግን ናሳ ጨረቃ ላይ እንዳላረፈ በማስረጃዎች እየተረጋገጡበት ነው።የዘመኑ ሳይነስም የፕላኔቶች ቁጥር አንዳንዴ ፱ አንዳንዴ ፲ እያደረጉት ነው።በተመሳሳይ አልበርት አንስታይን ስለ ጥቁር ሽንቁር (Black Hole) ጽንሰ ሓሳብ ከማስረዳቱ በፊት አባቶቻችን "መጽሐፈ ፀሐይ" በሚባል መጽሓፍ ዘርዝረውት ነበር።
ታድያ እኛ አሁን በምዕራባውያን የትምህርት ስርዓት ቁጥጥር ሥር ውለን እየሰለጠንን ይሆን ወይስ እየሰየጠንን ፧
ትንሣኤሽ ይናፍቀናል ኢትዮጵያ ።
✍ ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው።
No comments:
Post a Comment