ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በእውነት የተቃውሞ ትዕይት እያደረጉ ያሉት ዜጎች ለውጥ ፈልገው ነው ፧ የተቃውሞው መስረታዊው
መንስዔ ሰነ ቁጠባዊ ውድቀት መሆኑ ለውሸት ፍደሳ በተዘጋጁ መገናኛ ብዙሃን እየተነገረ ነው። “አንተ ምን አስጨነቀህ?” ለምትሉኝ እህትና ወንድሞቼ የምላቹ ቢኖር ነገሩ አልገባቹም። ዓለማችንን ለመቆጣጠር እየተጣደፉ ያሉት ሰላቢ እጆች (ኢሉሚናቲ) የመጨረሻዋ ዕቅዳቸው ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ማወቅ አለብን። በተጨማሪም ሰው እንደመሆናችን በስላሴ አምሳል የተፈጠረ ፍጡር ሁሉ በሚያደርገው ነገር ያገባናል። ቆይቶም የክፋትም ሆነ የበጎ ድርጊት ወላፈኑ እኛ ጋር መድረሱ እርግጥ ነው።
ወደ ተነሳሁበት ዋና ነጥቤ ልመለስ። በሀገረ ኢራን እየተደረገ ያለው የተቃውሞ ትዕይንት መነሻው የሰነ ቁጠባ መውደቅ መሆኑ የአለማችን ቁንጮዎች ቢነግሩንም ስሜት የሚሰጥ ምክንያት አይደለም። ምክንያቱም ሀገረ ኢራን ባለፉት ሁለት አመታት በአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ከተነሳላት በኃላ ከፍተኛ የሰነ ቁጠባ ዕድገት አስመዝግባለች።
በውጭ ጉዳይ ፖለቲካም ቢሆን ኢራን አይኤስን በማሸነፍ አሜሪካ በሶርያ የምትፈጸመው ሴራ በመጥኑም እንዲቀንስ አድርጋለች። የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ በመሰከሩላት ደረጃ የመካከለኛው ምስራቅ የበላይ ሀገር መሆንዋ አስመስክራለች። ይህም የአሜሪካ የ አረብ አለም ደጋፊና አጋር በሆነቺው ሳውዲ አረብያ በሽዓና ሱኒ የሙስሊም ፊታውራሪ ፍክክር ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። በዚህም ምክንያትም ሳውዲ አረብያና ኢራን በሀገረ የመን የእጃዙር ጦርነት እንዲያካሂዱ ሆኗል።
ሀገረ ኢራን በሰነ ቁጠባም ይሁን በፖለቲካው በተሻለ ሁኔታ ባለችበት ባሁኑ ወቅት ታድያ ለምን ዜጎችዋ ለተቃውሞ ተነሱ ፧ የተቃውሞው መነሻና
የሴራው አቀናባሪም ዳግማዊት ባቢሎንዋ የአውሬው ማደርያ ሀገረ አሜሪካ ነች። የሄግል ሰይጣናዊ ፍልስፍና በመጠቀም ሳዳም ሑሴንን በውሽት የአቶሚክ ቦምብ በመክሰስ የአለማችን አሸባሪዋ ሀገረ አሜሪካ እንዲገደልና ሃገሪቱም ሰላም እንዲርቃትና አሜሪካ ለምትፈጥራቸው የሽብር ቡድኖች መፈንጫ እንድትሆን ሆኗል። በመቀጠልም የሊብያው ጋዳፊ ራሱን ከአሜሪካ ባንኮች የገንዘብ ስርዓት ሀገሩ ሊብያ ነጻ በማውጣቱ በሸረበችለት ሴራ ህይወቱ እንዲያጣ ሊብያም የአሸባሪዎችና መናከርያና ለስደተኞች የምድር ሲዖል እንድትሆን አድርጓታል። በሀገረ ሶርያም እንዲሁ ህጻናት ያለ ሃጥያታቸው በአሜሪካን በሩስያ ፍክክር ምክንያት በየቀኑ በአየር ድብደባ የሚገደሉባት ሆናለች። ቀጣይዋ ተረኛ ደግሞ ኢራን ነች።
የኢሉሚናቲዎች ፊታውራሪ አሜሪካ ይህንን ሁሉ የምታደርገው የኢሉሚናቲዎች የመጨረሻው ግብ በሆነው አንድ የዓለም መንግሥት የመመስረት ጉዞ አንደኛው መንገድ ነው። ይህ እየሆነ ያለዉም እንደ ሞግዚት በምንትከባከባትና በጽዮናውያን (ኢሉሚናቲ) የሮዝስቻይልድ ቤተሰብ በተመሰረተቸው የአሁኗ የውሸት እስራኤል (የመጽሐፍ ቅዱስዋ እስራኤል አይደለችም) "ታላቅዋ እስራኤል"
የመመስረት ዕቅድ ነው።
ይህንን ሰይጣናዊ ዕቅድ ለማስፈጸም ኢራን በሰነ ምድር አቀማመጥም ሆነ በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የግድ የሃሰን ሩሃኒ መንግሥት በማስወገድ አሜሪካና እስራኤል መራሽ የሆነ ቡድን ወይም አካል ሀገሪትዋን በመቆጣጠር ታላቅዋ ሀገረ እስራኤል የመመሥረት ፍላጎት እውን ማድረግ ቀጣዩ እርምጃ ይሆናል።
ታድያ ይህ ሰይጣናዊ ዕቅድና ሴራ ለማስፈጸም ተጎጂ የሚሆኑት ንጹሃን ሰዎች (ህዝቦች)
እንጂ የዚህ የክፋት ድርጊት አስፈጻሚዎች (ደጋፊም ተቃዋሚም የሆኑት) አይደሉም። ይህም የኢሉሚናቲዎች ዋነኛው አካሄድ ነው።
ሰኞ ታኅሳስ 23, 2010 ዓመተ ምሕረት
No comments:
Post a Comment