EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 3 January 2018

የኢንዶሚን ምግብ የጤና ጉዳቶች


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ፈጣን ፓስታዎች በጣም ቀላል በሆነ ዝግጅት ምክንያት በመላው ዓለም የሚበሉ ተወዳጅ ምግቦች ናቸው። ነገር ግን ተጠቃሚዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር የጤና ችግር መኖሩ አለመኖሩ ላይ ከፍተኛ ውዝግብ ይነሳሉ።ከነዚህ ምርቶች አንዱ ከሃገረ ኢንዶኖዥያ ወደ ሃገራችን የሚገባው የኢንዶሚን ምርት ነው።ኢንዶሚን የሁለት ቃላት ጥምረት ሲሆን ኢንዶ የሚመረትበት ሃገር ኢንዶነዥያ ሲወክል ሚን ማለት ደግሞ ፓስታ ማለት ነው።

እነዚህ ለሰውነታችን ጎጂ የሆኑ የኬሚካል ስብስቦች እንድንጠቀም የሚያደርጉን ዘወትር በየመገናኛ ብዙሃኑ የሚሰራጩ አደናጋሪና ትኩረትን በመስረቅ ጭንቅላታችን ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ተገዢ የሚያደርጉን ማስታወቅያዎች ናቸው። ኢንዶሚን የምግብ ምርት ለሰውነታችን አላስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ከታች የሚገለጽ ይሆናል።

፩. የምግብ መሰራጨት - ከ፭ አመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ በሰውነት ላይ የሚካሄደው የምግብ ስርጭት ያጨናግፋል።

፪. ካንሰር -  በኢንዶሚን የሚገኝው "ስቴሮፎም" የተባለው ንጥረ ነገር የካንሰር በሽታ የሚያመጣ  ነው።

፫. የጽንሰ መጨናገፍ - በእርግዝናቸው ወቅት የኢንዶሚን ምርት የሚመገቡ ሴቶች በጽንሱ እድገት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚያደርስ ጽንሱ እንዲጨናገፍ ያደርገዋል።

፬. ትርኪምርኪ ይዘቶች - የኢንዶሚን ምርት በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረ ነገር ብቻ የያዘ ነው። ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑት ንጥረነገሮች ቪታሚንና ሌሎች ማዕድኖች የለዉም። ይህም ኢንዶሚንን ጥቅም አልቦ የትርኪምርኪ ስብስብ ያደርገዋል።
፭. ሶድዮም - ኢንዶሚን ከፍተኛ መጠን ባለው ሶድዮም ይሞላል። ይህም አዘውትሮ ኢንዶሚንን መመገብ የልብ በሽታ፣ የደም ግፊት እና የኩላሊት መጎዳት ያስከትላል።

፮. ሞኖ ሶድዮም ጉሉታሜት( MSG ) - ይህ ኬሚካል የኢንዶሚን ጣዕም ለመጨመር የሚጨመር ነው። ይህ ኬሚካል  አንዳንድ ሰዎች ላይ የሰውነት መቆጣት ( አለርጂክ) ያስከትላል። በተጨማሪም የራስ ምስታት የፊት መሸማረር የስቃይ ስሜትና የማቃጠል ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋል።

፯. ከመጠን በላይ ክብደት - ኢንዶሚንን አብዝቶ መመገብ ለከፍተኛ ውፍረት ይዳርጋል። በውስጥ ያለው የሶድዮም ንጥረ ነገር በሰውነታችን ያለው የውሃ መጠን እንዳይቀንስ በማድረግ ለከፍተኛ ውፍረት ያጋልጠነል። በመቀጠል የልብ ችግር ይከተላል።
፰. ምግብ መፍጨት - ኢንዶሚን የሰውነታችን የምግብ መፍጨት ስርዓት አስቸጋሪ እንዲሆን ያደርገውል። በማስከተል የብርድ ብርድ ማለት ስሜት እንዲፈጠር ያደርገዋል።

፱. ፕሮፍልሊን ግላይኮል - በኢንዶሚን የሚጨመር ቅመም ነው። ይህ ንጥረ ነገር ጥቅም ላይ የሚውለው እርጥበትን በማቆየት እርጥቡ ኢንዶሚን እንዳይደርቅ ስለሚከላከል ነው። ንጥረ ነገሩ የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅም ያዳክማል። ከመላው ሰውነታችን በመሰብሰብ በልብ ፣ ኩላሊትና ጉበት ይከማቻል። ይህም በጉሮሮ ላይ ጉዳት ያደርሳል።

፲. ምግብ መዋሃድ - ኢንዶሚን በምግብ መዋሃድ ላይም ችግር ይፈጥራል። ይህ የሚሆነው ሱስ  የሚያስይዙ ፣ ቀለም እንዲኖረው እና  እንዳይበላሽ ተብሎ የሚጨመሩ ብዙ ኬሚካሎች ስላሉ ነው።

No comments: