EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 3 January 2018

ሃገረ አሜሪካና አለማችን አሁን




ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

አሜሪካውያን የሚያስብዋት ዓለም
የሃገረ አሜሪካ ርዕሰ ስልጣን ባለቤት ዶናልድ ትራምፕ የዩኤስ አሜሪካ ኤምባሲን ከቴል አቪቭ ወደ የሃገረ እስራኤል ዋና ከተማ ናት ባልዋት ኢየሩሳሌም እንደሚያዛውሩ ካወጁ በኃላ የዓለም ምላሽ በጣም ግልጽ ነበር። የከፋ ትችቶችና ወቀሳዎች ነበር የቀረበባቸው። የተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ምክርቤት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማናት ብለው ያቀረቡት ሓሳብ ውድቅ አድርጎታል።

128 የምክር ቤቱ አባል ሃገራት የትራምፕ ሓሳብ ውድቅ ሲያደርጉት 35 ሃገራት ድምጽ ታቅቦ አድርገዋል። በአንድ ወቅት አለማችን በልግስና ፣ በጥበቃ ፣ በፈጠራና በአስተያየት የምትመራ ሃገር ነበረች አሜሪካ። ነገር ግን ይህ ሁሉ አሁን ተለውጧል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በዘመናት ፍጻሜ ላይ "የያዕቆብ ክብር ይደክማል" (ኢሳያስ ፲፯፡፬) ይላል።

የያዕቆብ ዘር የተባሉት ከምድረ እንግሊዝ ወደ አሜሪካና ወደ ምዕራብ አውሮፓ በመሄድ የሰፈሩት ናቸው። የጥንቶቹ ነቢያት አስቀድሞ እንደተናገሩት የዓለም ህዝቦች ከአሜሪካ ጎን እንደማይቆሙ ነው። እነዚህ ተመሳሳይ ትንቢቶች ዩኤስ (US) እና ሌሎች የእስራኤላዊያን ዘሮች (የያዕቆብ ልጆች) ከእንግዲህ "ራስ" አይሆኑም ፤ ነገር ግን "ጅራት" ይሆናሉ (ዘዳግም 28:13 እና 43-44 በንጽጽር ተመልከት ) እና ይህንን ዛሬ እየሆነ ነው!

ኢትዮጵያዊው ካህን መልከጸዲቅ የቆረቆራት ቅድስት ከተማ አሁን የጽዮናውያን የሄግል ፍልስፍና መተግበርያ እየሆነች ነው። ኢትዮጵያ በአልተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ቀጣፊዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሉት) ፍልስጤምም ሆነ እስራኤልን መደገፍ አልነበረባትም። ምክንያቱም ይህ የትራምፕ አዲስ የቁማር ጨዋታ ነበር።

ታኅሳስ 21, 2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: