EAR

አዲስ ነገር

Friday, 1 December 2023

ህወሓት | አሁንም የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ ስጋት

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ህወሓቶች ዲያብሎሳዊ ሤራቸው ከማንም በከፋ መልክ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከጠነሠሡ ቆይተዋል። ህወሓቶች የኔተንያሁን እና የሐማስ ፈለግና ስልት ተከትለው ነው “እንመራዋለን” በሚሉት ሕዝብ ላይ ለረጅም ጊዜ ይህን ያህል መከራና ስቃይ ያመጡበት። ዛሬም የክርስቲያን ሕዝባችን ደም ገና አላረካቸውም፤ ለቀጣዩ ዕልቂት እየተዘጋጁ ነው። ዛሬም በደምና መቅኒ የተነከረውን ባለ ቀይና ቢጫ የሉሲፈር/ቻይናን ሰንደቅ እያውለበለቡ የክርስቲያን ወገኔን ደም ለማፍሰስና ሉሲፈራውያኑ ሞግዚቶቻቸውን ለማስደስት ወደ አዲስ አበባ እና ጂቡቲ በመመላለስ ላይ ናቸው።

ህወሓቶች ሕዝባችን ዛሬም በረሃብ እያለቀ በሚገኝበት ወቅት የብሪታኒያ ሉሲፈራውያን በአውስትራሊያ በኩል የመለመሏቸውን 'አባ' ሰረቀ ብርሃንን 'አባ ሰላማ' ቅብርጥሴ እያሉ የሹመት ድራማ እንዲሠሩ በተዋናይነት መርጠዋቸዋል። የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ልጆች ቢሆኑና በጭፍጨፋው እጃቸው የሌለበት ቢሆን ኖሮማ ከሌሎች ጉዳዮች ይልቅ ስለ አክሱም ጽዮን ጭፍጨፋ በየዕለቱ ምርመራዎችን፣ መረጃዎችን ባቀረቡ ነበር። እንዲያውም ከማንም በልጠውና ከምንም ነገር በላይ ለዚህ እጅግ በጣም ብዙ ትኩረት ሊሰጠው ለሚገባው ጉዳይ አስቀድመው ጊዜ፣ ገንዘብ እና መስዋዕት መክፈል ነበረባቸው። አዎ! ዛሬም በራሳቸው ርዕዮት ዓለም ተጠምደዋል፣ አጀንዳ እየፈጠሩ የሉሲፈርን/ቻይናን ሰንደቅ ከማስተዋወቅ ሌላ ምንም በጎ ነገር አይሠሩም። ለተራበውና ለተጠማው ሕዝባችን እንጀራና ውሃ መግዢያ “ገንዘብ የለንም!” ይላሉ፤ ለዚህ የሕዝባችንን ደም በከንቱ እንዲፈስ ላደረገው የሉሲፈር ሰንደቅ ማምረቻ ግን ገንዘቡ ላለፉት ሦስት ዓመታት ለአንድም ቀን ጎድሎባቸው አያውቅም። እንዴ ዶሮ እንኳን ጫጩቶቿን ከቀማኛ ዘንዶ እና ንሥር እራሷን እስከ መሰዋት ድረስ እንዴት እንደምትከላከል እናውቃለን፤ እነዚህ አውሬዎች ግን ከየት እንደመጡ አላውቅም በተቃራኒው ሕዝብ አሳልፈው ይሰጣሉ!

No comments: